Tender Detail

Tender Details

  • Company City Government of Addis Ababa Office of the auditor General (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት)
  • Address ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ ከፊሊፕስ ህንፃ ከፍ ብሎ ከማይጨዉ ክሊኒክ ጀርባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ህንፃ ላይ 9ኛ ፎቅ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115-58-07-15
  • Websitehttps://www.aaag.gov.et/
  • Deadline28 Oct 2025, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • opening date2025-10-28 00:00:00
  • Categories Office Supplies And Services , Textile, Garment & Leather , Stationery Materials , Electronics Materials , Vehicle

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡


                                                                 የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

                                     መለያ ቁጥር 001/2018 ዓ.ም. 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ 

ሎት 1. የደንብ ልብስ ግዥና ስፌት

ሎት 2. የጽሕፈት መሣሪያዎች

ሎት 2 ልዩ ልዩ ኅትመቶች

ሎት 3. የተለያዩ የመኪና ዕቃዎች

ሎት 4. የኤሌከትሮኒክስ ዕቃዎች

ሎት 5 የአንቲቫይረስ ሶፍት ዌር

ሎት 6. የተለያዩ የቢሮ ፈርኒቸሮች

ሎት 7. የቢሮ መጋረጃ፣ የግድግዳ ልባስ ፓኔል፣ አልሙኒየም ፓርቲሽን ፍላይ ውድ እና መስታወት ሥራ እና የተለያዩ የበር እና የመሳቢያ ቁልፎች ሲሆኑ 

በጨረታውን መሣተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው

ሀ. ለሚጫረቱባቸው ዕቃዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣

ለ. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታከስ /NAT/፣ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ 

ሐ. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚጫረቱበትን ዕቃ የጠቅላላ ዋጋ 2% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ 

መ. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳደር እና ጠቅላላ አገልግሎት የሥራ ክፍል መግዛት ይችላሉ፡፡ 

ሠ. ናሙና ለተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ የሚጫረቱበትን ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

ረ. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን መ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር ላይ የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው በመሙላትና የድርጅታቸውን ማኅተም፣ ፊርማ በማሳረፍ እና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የጨረታው ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለዚሁ ጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። 

ሰ. ጨረታው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ ቆይቶ በከኛው ቀን ከቀኑ 3:30 ሰዓት ከታሸገ በኋላ በዕለቱ ከቀኑ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡ ሆኖም ከኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ 

ሸ. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ 

ቀ. ማንኛውም ተጫራች ዋጋውን በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡ 

በ. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0115-58-07-15 ወይም 0911-36-05-27 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ፡- ሜከሲኮ አደባባይ አካባቢ ከፌዴራል ፖሊስ ዋና መ/ቤት ወደ ልደታ ቤ/ን በሚወስደው መንገድ ትንሽ ከፍብሎ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ሕንፃ 9ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል 

                                                                  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር መ/ቤት

Save Tender