አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ አላቂ እቃዎች እና የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መፈጸም ይፈልጋል።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ አላቂ እቃዎች እና የተሽከርካሪ ጥገና ጋራዥ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ኮ/ዲ/ግ/ማ/ድ/ግ/ጨ/ቁ/03/2018
ድርጅታችን ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን እቃዎች ማለትም፡-
- ሎት 1. የአደጋ መከላከያና ደንብ ልብስ ዕቃዎች
- ሎት 2. የንጽሕና መጠበቂያ እቃዎች
- ሎት 3. የተሽከርካሪ ጥገና ለከባድ፣ ለቀላልና ለማሽነሪ ጋራዥ አገልግሎት ግዥ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም
- በዘርፉ የተሰማሩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል በኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት C.R.D.A አጠገብ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1፣ 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ ለሎት 2፣ 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ለሎት 3፣ 50,000 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantes) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአሥር ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በአሥራ አንደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በግዥ ዳይሬክቶሬት ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ:‐ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮንስትራከሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት ከሲ.አር.ዲ.ኤ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 011 4 62 14 57/ 0928 74 21 21
ኮንስትራክሽን ዲዛይን ግንባታ ማማከር ድርጅት
