የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር Promotional Materials &Corporate Gifts (EOI) A Digital Asset Production Services (TOR) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
CN/NCB/12/2018
የድርጅታችን ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ/የተ/የግል ማህበር Promotional Materials &Corporate Gifts (EOI) A Digital Asset Production Services (TOR) ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ተፈልጓል። በዚህም
ሎት 1፡- Promotional Materials & Corporate Gifts (EOI)
ሎት 2፡- Digital Asset Production Services (TOR) ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል። በመሆኑም ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ በጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችሉ የሚገልጽ ደብዳቤ፤ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡትን ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የምዝገባ ሰርተፍኬት፤ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እና የዕቃው ወይም የአገልግሎቱ ዝርዝር መግለጫ በተለየ በሰም በታሸገ ፖስታ እንዲሁም ዕቃዎቹን የምታቀርቡባቸውን ዋጋ በተለየ በሰም በታሸገ ሁለተኛ ፖስታ በማድረግ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
የጨረታ ዶክመንቱን ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ የግዢ ዋና ክፍል ብር 100.00 በመክፈል ከሰኞ እስከ ዓርብ (ጠዋት 2:00-6:00 እንዲሁም ከሠዓት 7:00-11:00) እና ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጠዋት ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ማስከበሪያ ሎት1፡- Promotional Materials & Corporate Gifts (EOI) ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) እና ሎት 2:- Digital Asset Production Services (TOR) ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ. ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከመጫረቻ ዶክመንት ጋር መቅረብ ይኖርበታል።
ተጫራቾች የመጫረቻ ዶክመንታቸውን ከላይ በተጠቀሰው አድራሻና የሥራ ሰዓት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓ.ም 4፡00 ጠዋት ድረስ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው በዚሁ ዕለት በ 4፡30 ጠዋት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመስብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል። ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ያላሟላ ተጫራች ያለተጨማሪ ማስታወቂያ ከውድድሩ ዉጪ ይደረጋል።
ድርጅቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃ.የተ.የግ.ማ
ቦሌ መንገድ ደንበል የገበያ ማዕከል ጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ
ዋና መ/ቤት ህንፃ 5ኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር 011-1-569992
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
