የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የሆኑ አሮጌ ጎማዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ኢ/ኤ/አ/አ/ሪ/ብሔ/ግ/ጨ/-005/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን የሆኑ አሮጌ ጎማዎች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው አይነት |
ሎት |
የሚገኝበት ቦታ |
የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታው መዝጊያ ቀን |
የጨረታው መክፈቻ ቀን |
|
|
አሮጌ ጎማዎች |
ሎት-1 |
አምቦ ከተማ |
40,000.00 |
ከህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 |
ከህዳር 03 ቀን 2018 ከቀኑ 8፡30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር (1000254843017 EEU Ambo District Connection Fes) የማይመለስ ብር 600 /ስድስት መቶ/ ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት አምቦ ከተማ የድሮ ሃዩሜ ኮሌጅ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር፡-14 አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት: ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ጎማዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን፣ እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት አምቦ ከተማ የዱሮ ሃዮማ ኮሌጅ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር፡- 14 አምቦ ሪጅን የአቅርቦት ሰንሰለት እና ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-2-00-97-77 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አምቦ ሪጅን
