የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ አልባሳት፤ የህክምና እቃዎች፤ የህትመት፤ የመኪና ጎማ፤ የGeneretor.Lift እና fire pump ጥገና (preventive Maintenance፤ የመኪና እጥበት እና ግሪስ፤ ዊል ባላንስ፤ አለይመንት እና የስረኛ ቀለብ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
የግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር YS/C/d NCB002/2018 ዓ/ም
የየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ለ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያውና ለተለያዩ የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የደንብ አልባሳት፤ የህክምና እቃዎች፤ የህትመት፤ የመኪና ጎማ፤ የGeneretor.Lift እና fire pump ጥገና (preventive Maintenance፤ የመኪና እጥበት እና ግሪስ፤ ዊል ባላንስ፤ አለይመንት እና የስረኛ ቀለብ በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም በማስፈለጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
|
ሎት |
የሚገዙ እቃዎች የሎት ዝርዝር |
በሲፒኦ የሚያዝ የገንዘብ መጠን |
|
ሎት1 |
የእስረኛ ቀለብ |
1000 |
|
ሎት2 |
የመኪና እጥበት እና ግሪስ |
1000 |
|
ሎት3 |
የመኪና ጎማ |
1000 |
|
ሎት4 |
የGeneretor.Lift & FirePump 79(Preventive Maintenance |
1000 |
|
ሎት5 |
ደንብ ልብስ |
500 |
|
ሎት6 |
ዊል ባላንስ እና አለይመንት |
1000 |
|
ሎት7 |
የህትመት ውጤቶች |
1000 |
|
ሎት8 |
የህክምና እቃዎች |
1000 |
|
ሎት9 |
የዳቦ መቁረጫ ማሽን |
1000 |
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ላይ ተቀባይነት የለውም።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ስም በተዘጋጀው በባንክ በተመሰከረለት
- ሀ የባንክ (CPO) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት 60 ቀን ነው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግ/ቤት ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የዕቃ ናሙና ከጨረታው መክፈቻ ቀን በፊት መቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች ሾላ ገበያ በሚገኘው በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ ላይ የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ እንዲሁም በ11ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 505 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። በ11ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛ ቢሮ ቁጥር 505 ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ከስራ ቀናት ውጪና የክብረ በአል ቀናት ከዋለ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ሲሆን ይከፈታል።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ካላንደር ወይም ስራ የማይኖርበት ከሆነ በቀጣዩ ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ
