በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በፑላችን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ ጽ/ቤቶቸ አገልገሎት የሚሰጡ የዓቃቤህግ ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የእንስሳት መድሀኒት፣ የእንስሳት ህክምና አላቂ እቃዎች፣ የዶሮ ኬጅ የ3 ወር ቄብ ዶሮዎች፣ ኮምፖስት እና ዘመናዊ የንብ ቀፎ ከነመንጋው፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ የፋ/አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ለ2018 በጀት ዓመት በፑላችን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ ጽ/ቤቶቸ አገልገሎት የሚሰጡ የዓቃቤህግ ባለሙያዎች ደንብ ልብስ፣ የእንስሳት መድሀኒት፣ የእንስሳት ህክምና አላቂ እቃዎች፣ የዶሮ ኬጅ የ3 ወር ቄብ ዶሮዎች፣ ኮምፖስት እና ዘመናዊ የንብ ቀፎ ከነመንጋው፣ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት መስፈርቱን ከምታሟሉ ተወዳዳሪዎች አገልግሎቱን ማግኘት ይፈልጋል።
- የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- የጨረታ ሰነዱን አራት ኪሎ በሚገኘው የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ በዋና ስራ አስፈጻሚ የፋ አስ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ 9ኛ ፎቅ 902 ቁጥር ጋዜጣው ከወጣበት ቀን 2018 ዓ.ም እስከ አስረኛው የስራ ቀን 2018 ዓ.ም ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ፎቶ ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀን የማይመለስ 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በማዘጋጀት እና በማሸግ አራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ቢሮ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ እስከ 11ኛው የስራ ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ በአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በዋና ስራ አስፈፃሚ የግዥ ቡድን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል።
- ተጫራቾች የጫረታ ማስከበሪያ ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/ በየዘርፉ በሲፒኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ፣ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ከጨረታው ይሰረዛል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አሸናፊ ድርጅት የውል ማስከበሪያ የአጠቃላዩን ብር 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል
- በጥቃቅን ተደራጅተው በዘርፉ ለተሰማሩ ተጫራቾች የተገለጹትን ቁሳቁሶች እቃዎች የአምራችነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤ ይህ ካልሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛት እና የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
የአራዳ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ የአስ/ፋ/ጽ/ቤት የግዥ ቡድን