የመንግስት ሠራተኞት ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር የምዕራብ ሪጅን ጽ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት በሥሩ ለሚገኙ ቅ/ጽ/ቤቶችና ለመስክ ጽ/ቤቶች የኤሌክትሮኒክስ ጥገና፣ የእጥር እና የቤት ጥገና እጅ ዋጋ፣ የደንብ ልብስ ስፌት እጅ ዋጋ፣ የጭነት አገልግሎት፣ የሥልጠና መስተንግዶ፣ የተሽከርካሪ እና ሞተር ሳይክል ጥገና፣ ቋሚ ዕቃዎች ግዥ፣ የህትመት ሥራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ስለዚህ ተወዳዳሪዎች፡-
- በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤ በሃገር ውስጥ ገቢ የድጋፍ ደብዳቤ የአቅራቢዎች የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የቫት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) በመክፈል ከቢሮ ቁጥር 7 (ሰባት) በመውሰድ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ እስከ 11፡00 ሰዓት የጨረታ ሠነድ ዋጋቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ በሁለት ኮፒ በማሸግ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜ /እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጎልም፡፡
- ተጫራቾች ባሸንፉት የዕቃ ዋጋ ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ የአሰራር ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ምስራቅ ወለጋ ዞን ፖሊስ መመሪያ ፊት ለፊት ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0576612054/0576615178
የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ምዕራብ ሪጅን