የሀዋሳ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የተለያዩ ዓይነት ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01
የሀዋሳ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በቀረበው ዝርዝር መሰረት የተለያዩ ዓይነት ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት- 2 - ኤሌክትሮኒክስ
- ሎት - 4 - ቴሌቪዥን እና ኮምፒውተር
- ሎት - 6 - ፈርኒቸር
- ሎት- 7 - ጋርመንት
- ሎት-17 - Agro processing
ጨረታውን መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፡፡
- የጨረታ ሰነድ ሀዋሳ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ እያንዳንዱን ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 (ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ዶክመንት ሞልተው ኦርጂናልና ፎቶ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ ላቀረቡት 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (ጥሬ ብር) ከኦርጂናል ዶክሜንት በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ሀዋሳ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ስም መሰራት አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ወቅት ማሟላት የሚገባቸውን ነገሮች አሟልተው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- አሸናፊው እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለተሸናፊ ወዲያውኑ የሚመለስ ይሆናል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች ጥራታቸውና ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ አስራ አምስት ቀናት (እሁድና ቅዳሜን ጨምሮ) ውስጥ ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን በአስራ ስድስተኛው ቀን ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- ጨረታውን ያሸነፈው ድርጅት አካል ዕቃውን በኮሌጁ ባለሙያ ተረጋግጦ ንብረት ክፍል ገቢ ሲያደርግ ብቻ ክፍያው የሚፈፀም መሆኑን ጭምር እንገልፃለን፡፡
- ጨረታውን የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀን በዓል ከሆነ ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ ቀን 5፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 10 ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/የሥራ ሂደት ክፍል ይከፈታል፡፡
- ዋጋ የሚሞላው ከኮሌጁ በገዛችሁት ሰነድ ላይ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0928982927 ወይም 0913038349
የሀዋሳ ተግባረ-ዕድ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
