ለመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፤ ቧንቧና መገጣጠሚያ፣ የውሃ ቆጣሪዎች፣ የውሃ ቧንቧ መስሪያ ዕቃዎች (Tools) የኤሌክትሪክ ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ቴሌቭዥን፤ የላብራቶሪ ዕቃዎች (Laboratory) ፓምፕ /Pump/፤ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ቢል ፕሪንተር፣ የቢሮ ወንበሮች /Furniture/ ማውንቴን ሳይክል፣ የባጃጅ ስፔር ፓርት እና ባለ ሶስት እግር ደረቅ ጭነት ወይም ባለ አራት እግር ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ለመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በ 2018 በጀት ዓመት የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ፣ መሳሪያ፣ የፅዳት ዕቃ፤ ቧንቧና መገጣጠሚያ፣ የውሃ ቆጣሪዎች፣ የውሃ ቧንቧ መስሪያ ዕቃዎች (Tools) የኤሌክትሪክ ዕቃ፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ቴሌቭዥን፤ የላብራቶሪ ዕቃዎች (Laboratory) ፓምፕ /Pump/፤ ኮምፒውተር፣ ፕሪንተር፣ ቢል ፕሪንተር፣ የቢሮ ወንበሮች /Furniture/ ማውንቴን ሳይክል፣ የባጃጅ ስፔር ፓርት እና ባለ ሶስት እግር ደረቅ ጭነት ወይም ባለ አራት እግር ደረቅ ጭነት ተሽከርካሪ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ከዚህ በታች የተገለፀውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶች እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ግብር የከፈሉ፡፡
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN Number) ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለፀውን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም መሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
- የሚገዙ ዕቃዎች በተሰጠው እስፔስፊኬሽን መሰረት አሟልቶ ላልቀረበና ማንኛውንም ስህተት ቢፈፅም ኃላፊነቱ የተጫራቹ /የአቅራቢው/ ድርጅት ይሆናል።
- ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ የሚቀርበው ዋጋ በግልፅ መፃፍ ይኖርበታል። እንዲሁም የመቂ ከተማ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ መሞላት አለበት፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ) የCPO ቼክ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ሰነድ ላይ ያቀረበው ዋጋ ለሶስት (3) ወር ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን የዋጋ ለውጥ የሚካሄደው ከሶስት ወር በኋላ በገበያ ጥናት አሸናፈው ድርጅት በሚያቀርበው ዋጋ ተንተርሶ በሚስጢ ዋጋ ይሆናል።
- አሸናፊው ድርጅት ውል በገባ በ 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዕቃውን በድርጅቱ መስሪያ ቤት ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ሙሉ በሙሉ ኦርጅናል መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰንዱን የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ቴክኒክና ፋይናንስ በተናጠል በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን የድርጅቱን ማህተም ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱ ማስታወቂያው ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር (10) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ11ኛው (አስራ አንደኛው) የስራ ቀን በ 6፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- አሸናፈው ድርጅት ባሸነፈባቸው ዕቃዎች ከጠቅላላ ዋጋ 10/100 ለድርጅቱ ውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች በአካል ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ከዚህ በላይ በተገለጸው መሰረት ተጫራቾች የጨረታ ግዴታ ባይወጡ ወይም ውሉን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘውን ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ በግዥ መመሪያ ቁጥር 02/2001 እና FA 1/2009 እንዲሁም እዋጅ ቁጥር 157/2002 መሠረት ጽ/ቤቱ ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ማወቅ ይኖርበታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡-
- የሚፈለገው የዕቃ ብዛት የምናሳወቀው የማሸነፊያ (የጨረታ) ዋጋ ከተለየ በኋላ መሆኑን እንገልጻለን።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ዋጋ ከቫት ጋር መሆኑን እና ያለመሆኑን የጨረታ ሰነዱ ላይ በግልጽ መፃፍ ይኖርበታል።
- ለበለጠ መረጃ በሞባይል ቁጥር 0912999499 ወይም 0912309452 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አድራሻ፡- ምሥራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ የመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
የመቂ ከተማ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
