በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት 2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
2ኛ ዙር ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት አመት 2ኛ ዙር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት1. አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ ሎት2. የደንብ ልብስ፤ ሎት3.ጽዳት እቃ፤ ሎት4.የመስተንግዶ አገልግሎት ፣ሎት5. የቢሮ ዕቃዎች ጥገና የእጅና የማቴሪያል ዋጋ ጨምሮ ለየብቻው ይቀመጥ ፤ ሎት6. የሰራተኛ ካፌ መስተንግዶ ፣ ሎት 7.G.4 የወረዳው ህንፃ ቀለም ቅብ የእጅና የማቴሪያል ዋጋን ጨምሮ ለየብቻው ይቀመጥ፡፡ ሎት8. የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣ ሎት 9. የመኪና ጎማ፣ ሎትıo, የስፖርት ትጥቅ፣ በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. ከላይ ከተራ ቁጥር 1-10 ለተጠቀሰው ዕቃ በዘርፉ ሕጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤
2. የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፣
4. ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤
5. ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢዎች ዝርዝር ድረ ገጽ www.ppa.gov. et ላይ የተመዘገበ መሆኑን የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራች መሞላት ያለባቸው ከፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተምና ፊርማ ተደርጎበት ሙሉ ሰነዱ መመለስ አለበት፡፡ ሰነዱን ያልመለሰ ተጫራች ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
7. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ1o ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከዊንጌት ወደ አጠናተራ በሚወስደው መንገድ ብስራት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ እ/ከ/ከ/ከ ወረዳ 13 አስተዳደር 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-17 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመገኘት ብር300 /ሶስት መቶ ብር/በመከፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎቶች በ0.5% የተሰላ ሲሆን ሎት1. 2,000 ( ሁለት ሺህ ብር) ፤ ሎት2. 2.000( ሁለት ሺህ ብር) ፣ ሎት3. 2,500 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር) ፤ ሎት4. 3.000 (ሶስት ሺህ ብር) ፣ ሎት5. 1,500(እንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ፤ሎት6 5.000(እምስት ሺህ ብር) ፤ ሎት7 12,487 (አስራ ሁለት ሺህ አራት መቶ ሰማኒያ ሰባት)፣ ሎት 8. ኤሌክትሮኒከስ እቃዎች 2,000(ሁለት ሺህ ብር) ፣ ሎት9. 1000(አንድ ሺህ ብር) ፣ ሎት 10, የስፖርት ትጥቅ 1,500(አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ፤ ከታወቀ ባንከ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ ጨረታዉ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 10ኛው ቀን 11:30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
9. ተጫራቾች እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለጽ በታሸገ ኤንቨሎፕ
ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ ከዊንጌት ወደ አጠና ተራ በሚወስደው መንገድ ከብስራት 1ኛ ደረጃ ት/ቤት አጠገብ አ/ከ/ከ/ከተማ ወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር-17 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
10. ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰውን ዕቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ፡፡
11. ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ የዕቃውን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት የለውም፡፡
12. የጨረታ ሰነድ ማስረከቢያ የመጨረሻው ቀን በ1ዐኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር-17 ውስጥ ይሆናል፡፡
13. ቀጣዩ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተራ ቁጥር 12 በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ተፈፃሚ ይደረጋል ፡፡
14. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
15. በጥቃቅን የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጁበትን ዘርፍ በግልጽ የተቀመጠና አምራች ከሆነ የሚያመርተው ዘርፍ በግልጽ የተቀመጠና ደብዳቤውን ለመፈረም ስልጣን በተሠጠው አካል የተፈረመና የዋስትና ደብዳቤው ለጨረታ ማስከበሪያና ለውል ማስከበሪያ ማምጣት አለባቸው፡፡
16. አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም፡፡
17. የጨረታ አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውንም ለማቅረብ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ፡፡ ጨረታውን ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸንፉበትን ዋጋ 10% c.p.o የውል ማስከበሪያ አሰርተው መምጣት አለባቸው::
18. አሸናፊ ተጫራች ውል ከወሰደ በኃላ እቃውን በተቋሙ ንብረት ከፍል ድረስ በራሱ ትራንፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
19. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ-፡ ቋሚ እቃዎች ተጫራቾች ጽ/ቤቱ ባስቀመጠው ስፔስፊኬሽን መሰረት አስቀድሞ ከሰነዱ ጋርየእቃውን ፎቶ ማስገባት አለባቸው:: ከተቀመጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ የሚቀርብ ዕቃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የሁሉንም ሎቶች ስፔስፊኬሽን (ፍላጎት መግለጫ) በጨረታ ሰነዱ በክፍል ስድስት(6) ማየት ይቻላል፡፡
2. የቢሮ እቃዎች ጥገና እና የህንጻ ቀለም ቅብ ላይ በተቀመጠው የዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ላይ የእጅና የማቴሪያል ዋጋ ለየብቻው መቀመጥ አለበት፡፡ ስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-99-40
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የወረዳ 13 ፋይናንስ ጽ/ቤት
