Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያዩ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 17/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

 

የሐዋሳ ጉምሩ //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያዩ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች፣ አልባሳትና ጨርቃጨርቅ የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይ አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200 እስከ 600 ከሰዓት 700 እስከ 1100 ሰዓት፣ ቅዳሜ 200 እስከ-600 ሰዓት ድረስ በቅ//ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት በተጫራቹ ስም መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ስም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5 (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O. በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ለሀራጅ ጨረታ ለየመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) (CPO) ዋስትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 405 ሰዓት ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ///ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ሂደቱ ካለቀ 10 ደቂቃ በኋላ የሐራጅ ጨረታው የሚጀምር ይሆናል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል /እሁድ/ ቀን የሚዉል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የሥራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቬሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸውከዚህ ሰነድ ወጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ // ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።
  6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም። በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ //ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም።
  9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል።
  10. ተጫራቾች የዕቃዉን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፤ በተጨማሪ /ቤቱ የማይነበብ የሰነድ ኮፒ የመቀበል ግዴታ የለበትም፡፡
  11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው
  12. አሸናፊው ተጫራ ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል። ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃ ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
  13. //ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/ 046-212-65-95 ጠይቁ።

 

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት

Save Tender