በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የተተው ዕቃዎች ግልፅ ጨረታ ቁጥር ግ13/2018
በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/2011 መሰረት የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም WIRE DRAWING POWDER & WIRE DRAWING DIES: BLANKET, VACUM FLASK 2 LITTER, ADULT SHOE NIKE BRAND & OTHER ELECTRICAL CABLE, AIR FILTER, GASKETSET & OTHER POLYESTER FIBER NON WOVEN INTERLING HEALD FRAME OR HURNESS FRAME: የተለያዩ አልባሳት፣ BABY HAT፣ SCHOOL BAG, FABRIC ADULT CAP & SUPER MARKET SHELF MATERIAL: እና MEN SPORT SHOES BRAND እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ሲሆን አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ከኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶችን በአካል ለመመልከት ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 እስከ ቀኑ 10፡30 እና ዓርብ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ 5፡00 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡30 እስከ ቀኑ 10፡30 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 2፡00 እስከ ቀኑ - 5:30 መመልከት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱን ከኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም /ድረገፅ/ ኦንላይን ላይ ብቻ መግዛት እና መጫረት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ በኦከሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ማያያዝ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆኑ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በ ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ፤ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች ብቻ አሰርተው ኦክሽን ኢትዮጵያ ሄደው በማስያዝ ወይም በአክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ባለው የሲፒኦ አማራጮች ኦንላይን ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ አሰቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሎት ዋጋ ቅ/ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወሰድም፡፡ በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፤ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም።
- ተጫራች የኦከሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) - ብለው በማውረድ ወይም (auction.et] ላይ መመዝገብ እና መጫረት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 8ኛው የሥራ ቀን 02/04/2018 ከጠዋቱ 5፡00 ድረስ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን ፕላትፎርም መወዳደሪያ ዋጋ ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታውን ሂደትና ውጤት ኦንላይን መከታተል ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያስገቡት ዋጋ 15% ቫትን ያካተተ መሆን አለበት፡፡
- ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተጀመረ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፣ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ጨረታው ተጀምሮ ዋጋ ከሰጡ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
- የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ በ5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገበ ይደረጋል።
- በተራ ቁጥር 10 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ/ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው በ2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡
- ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ለጨረታ ያቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው። በጨረታ ተሸጦ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡
- የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመለከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በአጭር ስልክ ቁጥር መስመር 9164 ወይም 09-05-11-55-11/011-666-8828 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡-
በስልክ ቁጥር 022-236-90-94 /022-236-01-90 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
