በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስና ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ለ3ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
3ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 003/2018
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስና ጽ/ቤት በስሩ ላሉት ጽ/ቤቶች በ2018 በጀት ዓመት ለ3ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳደሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ፣ ሎት 3 የፅዳት እቃ፣ ሎት4 የመስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 5 ለህንፃ ለቁሳቁስ እቃዎች፣ ሎት 6 የስፖርት ትጥቅ፣ ሎት 7 የአይሲቲ እቃዎች፣ ሎት 8 G+4 የወረዳው ህንፃ ቀለም ቅብ የእጅና የማቴሪያል ዋጋን ጨምሮ ለየብቻው ይቀመጥ፣ ሎት 9 ቋሚ እቃዎች ጥገና፣ ሎት 10 ትራንስፖርት አገልግሎት፣ ሎት 11 የጓሮ አትክልት ዘር በዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፋ ይጋብዛል።
ስለሆነም፡-
- ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ለተጠቀሰው እቃ በዘርፉ ህጋዊና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- ቫት ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- ቲን ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆኑን በአቅራቢነት ዝርዝር ድረገፅ www.ppa.egp.et ላይ የተመዘገበ መሆኑን የሚረጋገጥ ይሆናል።
- ተጫራቾች የገዙትን መደበኛ የጨረታ ሰነድ በተጫራቶች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በአግባቡ ተሞልቶና በድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ሙሉ ሰነዱ መመለስ አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 እሸት ት/ቤት ጀርባ 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 ፋይናንስ ጽ/ቤት በመገኘት ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይቻላል።
- ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ሎት 0.5 % የተሰላ ሲሆን ሎት 1 አላቂ የቢሮ እቃዎች 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር)፣ ሎት 2 የደንብ ልብስ ሎት 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)፣ ሎት 3 የፅዳትእቃ 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፣ ሎት4 የመስተንግዶ አገልግሎት 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፣ ሎት 5 ለህንፃ ለቁሳቁስ እቃዎች 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፣ ሎት 6 የስፖርት ትጥቅ 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)፣ ሎት 7 የአይሲቲ እቃዎች 2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)፣ ሎት 8 G+4 የወረዳው ህንፃ ቀለም ቅብ የእጅና የማቴሪያል ዋጋን ጨምሮ ለየብቻው ይቀመጥ፡፡ 10,000.00 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት 9 ቋሚ እቃዎች ጥገና 3,000.00 (ሶስት ሺህ ብር)፣ ሎት 10 ትራንስፖርት አገልግሎት 2,500.00 (ሁለት ሺህ አምስት መቶ ብር)፣ ሎት 11 የጎሮ አትክልት ዘር 1,500.00 (አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር) ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የተረጋገጠ CPO ብቻ ከዋጋ ማቅረቢያ ሰነዱ ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው ከወጣበት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች እያዳንዱን የሚሸጡትን ነጠላ ዋጋና የጠቅላላውን ዋጋ ከነቫቱ በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውንና የጨረታውን አይነት በመጥቀስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 20 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።
- ተጫራቾች በዘርፋቸው የተጠቀሰውን እቃ በሙሉ መጫረት ይችላሉ።
- ሁሉም ተጫራቾች ሰነዱን ሞልተው ሲያስገቡ የእቃዎችን ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡ ናሙና ካላቀረቡ ተቀባይነት የለውም።
- የጨረታ ማስከበሪያ የመጨረሻው ቀን በ10ኛው ቀን እስከ ቀኑ 11፡30 ሰዓት ሲሆን ጨረታው የሚከፈተው በ11ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በእለቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፋይናንስ ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 20 ውስጥ ይሆናል።
- ቀጣይ ቀን የስራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተራ ቁጥር 12 በተጠቀሰው ሰዓና ቦታ ተፈፃሚ ይደረጋል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
- በጥቃቅን የተደራጁ አካላት የሚያቀርቡት የዋስትና ደብዳቤ የተደራጀበትን ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና አምራች ከሆነ የሚያመርተው ዘርፍ በግልፅ የተቀመጠና ደብዳቤውን ለመፈረም ስልጣን በተሰጠው አካል የተፈረመና የዋስትና ደብዳቤው ለጨረታ ማስከበሪያና የውል ማስከበሪያ መምጣት አለባቸው።
- አንድ ተጫራች ሌላው በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ማቅረብ አይችልም።
- የጨረታው አሸናፊነቱ ሲረጋገጥ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጌዜ ገደብ ውል ለመዋዋል ፈቃደኛ የሆነ እና እቃውን ለማቅረብ በግዥ ደንብና መመሪያ መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለማቅረብ ፈቃደኛ የሆነ ጨረታውን ተወዳድሮ አሸናፊው ከታወቀ በኋላ ውል ለመዋዋል ሲመጡ ያሸነፋበትን ዋጋ 10% CPO ውል ማስከበሪያ አሰረተው መምጣት አለባቸው።
- አሸናፊው ተጫራች ውል ከወሰደ በኋላ እቃውን በተቋሙ ንብረት ክፍል ድረስ በራሱ ትራንስፖርት የማቅረብ ግዴታ አለበት ።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ከተቀመጠው ስፔስፊክሽን ውጪ የሚቀርብ እቃ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ የሁሉንም ሎቶች (ፍላጎት መግለጫ) በጨረታ ሰነዱ በክፍል 6 ማየት ይቻላል።
አድራሻ፡- በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ኳስ ሜዳ እሸት ት/ቤት ጀርባ ወረዳ 9 አስተዳደር ህንጻ 2ተኛ ፎቅ
ስልክ ቁጥር፡- 011-2-30-41-01 / 011-2-75-90-43
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፋይናንስና ጽ/ቤት
