Tender Detail

Tender Details


የደ/ም/ኢ/ህ/ክ/መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፣ በሎት1 ጀኔራል ሜታል ፋብርኬሽን፣ ፕላምፕንግ እቃዎች እና ፈርኒቸርሜከንግ እቃዎችን/፣ በሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ በሎት 3. አይሲቲ ዕቃዎች በሎት4 አግሮፕሮሰስንግ፣ በሎት 5 ሆቴልና ቱሪዝም፣ በሎት 6 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ በሎት 7፣ አውቶሞቲቭ እቃዎች፣ በሎት 8 የጋርሜንት እቃዎች እና በሎት 10 ሰርቬይንግ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ PTC 001/2018

 

የደ/////መንግስት ካፋ ዞን ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2018 / በጀት ዘመን ለስልጠና አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎችን ማለትም፣ በሎት1 ጀኔራል ሜታል ፋብርኬሽን፣ ፕላምፕንግ እቃዎች እና ፈርኒቸርሜከንግ እቃዎችን/ በሎት 2. የጽህፈት መሳሪያ እና የጽዳት ዕቃዎች፣ በሎት 3. አይሲቲ ዕቃዎች በሎት4 አግሮፕሮሰስንግ፣ በሎት 5 ሆቴልና ቱሪዝም፣ በሎት 6 የኤሌክትሪክ እቃዎች፣ በሎት 7 አውቶሞቲቭ እቃዎች፣ በሎት 8 የጋርሜንት እቃዎች እና በሎት 10 ሰርቬይንግ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

ስለሆነም ተወዳዳሪዎች፡-

1 በሙያ መስክ ወይም በዘርፉ የተመዘገቡና ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው፣ ህጋዊ ዕቃ አቅራቢ ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይ ስለመሆናቸው እና የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2 የዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ /specification/ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ከ1ኛ ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀናት አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ መግቢያ በር እና በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግዥ ንብ/አስ/ ቢሮ 2 ፎቅ በአካል በመቅረብ በኮሌጁ የሂሳብ ቁጥር1000029122877 ላይ የማይመለስ 200 ብር በማስገባት የመጫረቻ ሰነዱን መውሰድ

3 ተጫራቾች ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት የሚጫረቱባቸውን እቃዎች በመለየት በአይነታቸው እያንዳንዱን የሚሸጡበትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ዋናውና ኮፒውን በፖስታ በማሸግ የሚጫረቱበትን ዘርፍ የተጫራቾችን ስም ወይም ድርጅት በመፃፍና ማህተም በመምታት ለዚሁ ተግባርበተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በሰዓቱ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4 የጨረታ ሳጥን የሚታሸገው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት 16ኛው ቀን የጨረታ ሰነዱን ከአ/አበባ የገዛችሁት አዲስ አበባ ሜክሲኮ አካባቢ በሚገኘው ተግባረእድ ፖሊ ቴክኒክ በግቢያ በር ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከረፋዱ 400 የሚታሽግ ሲሆን ከቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጨረታ ሰነድ የገዛችሁት ተጫራቾች ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቀን በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚታሸግ ሆኖ፤ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ጨረታው ከታሽገበት 2ኛው ቀን በቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 2ኛው ፎቅ ግዥ/ ንብ/አስ/ ቢሮ ከረፋዱ 400 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በጨረታ መዝግያና መከፈቻ ወቅት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪል ያለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አይከለከልም፡፡ እለቱ የእረፍት ወይም በዓል ቀን ከሆነ ወደየሚቀጥለው ስራ ቀን ይተላለፋል፡፡

5 ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ፣ የባንከ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ከሬዲት ለያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡

6 አሸናፊዎች ባሸነፉበት የዕቃ ዋጋ መጠን የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ የተረጋገጠ CPO የባንክ ዋስትና ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሌተርኦፍ ክሬዲት ለያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማወዳደርያ ሰነድ ለየብቻ ማስያዝ እና ያሸነፉበትን የእቃ ናሙና ውል ከገቡበት 3 /ሶስት/ ቀን ውስጥ ለኮሌጁ ቀድሞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ በጨረታ የተሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡

7 አሸናፊ ተጫራቾች ዕቃውን እስከ ቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ድረስ የትራንስፖርትና ማንኛውን ወጪ በመቻል በውሉ ላይ በሚጠቀሰው ቀን ማቅረብና ማስረከብ አለባቸው፡፡ ለማያቀርቡት ለውል ማስከበርያ ያስያዙት ገንዘብ አይመለስም፡፡

8 ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከተከፈተበት እለት ጀምሮ 60 ቀናት ይሆናል፡፡

9 በጨረታ ሰነዱ ላይ ማንኛውንም ማስተካከያ ማድረግም ሆነ ከቀረበው ሰነድ ውጭመሙላት አይፈቀድም

10 ተጫራቾች ባሸነፉበት እቃ የካሽ ሪጅስተር ደረሰኝ ከአታችሜንት ጋር አያይዞ ማቅረብ ወይም የካሽ ሪጅስቴር ደረሰኝ የማይጠቀሙ ከሆነ የማይጠቀሙበት ምክንያት ከገቢዎች /ቤት ደብዳቤ በማስደገፍ የእጅ በእጅ ደረሰኝ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፡፡

11 ኮሌጁ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0917916439 /0913466023 /0927694591/ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

 

የደ/////መንግስት በካፋ ዞን የቦንጋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ

Save Tender