በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 07 አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 02/2018 ማለትም ሎት 01 ደንብ ልብስ፣ ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 03 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 04 የቋሚ እቃዎች፣ ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 6 የጉልበትና ጭነት አውራጅ ጫኝ አገልግሎት በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ወረዳ 07 አስተዳደር ለ2018 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 02/2018 ማለትም ሎት 01 ደንብ ልብስ፣ ሎት 02 አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ ሎት 03 የጽዳት እቃዎች፣ ሎት 04 የቋሚ እቃዎች፣ ሎት 5 የመስተንግዶ አገልግሎት፣ ሎት 6 የጉልበትና ጭነት አውራጅ ጫኝ አገልግሎት በሁለተኛ ዙር ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ፡- ለሎት 01 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)፣ ለሎት 02 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት 03 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ለሎት 04 40,000 (አርባ ሺህ ብር)፣ ለሎት 05 10,000 (አስር ሺህ ብር)፣ ሎት 6 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በእያንዳንዱ ሎት በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ ለየብቻ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል በዚህም መሰረት፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው።
- የሚያቀርቡት የዋጋ ማቅረቢያ ላይ ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ፖስታዎች በእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ኮፒ በማለት በላያቸው ላይ ማህተም መደረግ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በእያንዳንዱ ሎት ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ሰነዱን ፋይናንስ ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 01 ቀርበው መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ አየር ላይ ውሎ በ11 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻው ቀን ባለመገኘታቸው ጨረታውን አያስተጓጉለውም።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ /ፖስታ/ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያ CPO ኦርጅናል ሰነድ ላይ በእያንዳንዱ ሎት ላይ በማስገባት በግዥ ክፍል ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01፣ ለሎት 2፣ ለሎት 3፣ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ለሎት 4፣ 5 በቀረበው ፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል።
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤት እስቶር ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የጨረታ ማስከበሪያ CPO ብቻ በባንክ በተረጋገጠ አሰርቶ መምጣት አለበት።
አድራሻ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ወረዳ 07 አስተዳደር ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ ካድስኮ አዋሽ ባንክ ጀርባ 100 ሜትር ገባ ብሎ።
ለተጨማሪ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0118 886 532 / 0118 885 787 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 07 ፋይናንስ ጽ/ቤት
