በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ በ2018 ዓ/ም በመደበኛ በጀት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- የትምህርትና ሥልጠና ዕቃዎች ግዥ
- የቢሮ የፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ
- የጽሕፈት መሣሪያ እቃዎች ግዥ
- የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
- የተሽከርካሪዎች ግዥ
- የደንብ ልብስ ግዥ እና
- ለሆቴል አገልግሎት የሚውሉ ዕቃዎች ግዥ ሲሆን
ሁሉም የተጠቀሱት ዕቃዎች ደረጃቸውን የጠበቁ መሆን ይገባቸዋል። ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፤ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ቲን ነምበር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በማረቆ ልዩ ወረዳ ቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ግዥና ንብ/አስ/ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 15 በአካል ቀርቦ መግዛት ይችላሉ።
የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) በቆሼ ኮንስትራከሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ አሸናፊዎች ያሸነፉትን እቃዎች ናሙና /ሳንፕል ማቅረብ አለባቸው።
- ተሸናፊ ተጫራቾች (ድርጅቶች) ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃዎች ቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን ለየ ብቻ በማሸግ ሙሉ አድራሻቸውን በመግለፅ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ፡- 046 465 06 72 / 09 10 47 31 34/ 09 12 40 62 68
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የማረቆ ልዩ ወረዳ የቆሼ ኮንስትራክሽንና ኢንዱስትሪያል ኮሌጅ
