በአ/ከ/ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
የ2018 ዓመት 2ኛ ዙር ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- አ/ከ/ክ/ከ/ወ/5/ፋ/ጽ/የጨ/ቁ/002/18 ቀን፡- 9/4/2018 ዓ.ም
በአ/ከ/ክ/ከተማ የወረዳ 5 ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለተለያዩ ሴክተር ጽ/ቤቶች ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
ከጠቅላላ ዋጋ የሚያሲዙት የብር መጠን |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
15,000.00 |
|
ሎት 2 |
ቋሚ ዕቃዎች |
20,000.00 |
|
ሎት 3 |
የቢሮ አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች |
9,628.00 |
|
ሎት 4 |
አላቂ የፅዳት ዕቃዎች |
26,000.00 |
|
ሎት 5 |
የቢሮ መስተንግዶ |
25,000.00 |
|
ሎት 6 |
የልብስ ስፌት |
20,000.00 |
|
ሎት 7 |
የተለያዩ የሕትመት ሥራዎች |
5,000.00 |
|
ሎት 8 |
የመድረክ የዲኮር ሥራ |
10,000.00 |
በመሆኑም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
- የዘመኑ ግብር ከፍለው የታደሰ ንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና የግብር መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የቫት /TN NO/ ተመዝጋቢ የሆኑና በአቅራቢዎች ዝርዝር በዌብ ላይት ስለመመዝገባቸው መረጃ የምናይ መሆኑን
- ተጫራቾች ለመወዳደር የጨረታ ሰነድ ስታስገቡ ለተወዳደራችሁበት አላቂ ዕቃ እና የልብስ ስፌት ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ /CPO/ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 0.5% በማስላት በማስያዝ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።ይህን ካላቀረቡ ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በማይመለስ ብር በካሽ 200.00 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል በወረዳ 5 ፋ/ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ወደ ቢሮው ሲገቡ በስተቀኝ በመግባት መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ሠነዱ በተጫራቾች መሞላት ያለባቸው ክፍሎች በሙሉ መሞላት አለባቸው።
- በሥራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ በራሳችሁ ምርት ላይ ልዩ አስተያየት ስለሚደረግ አምራች መሆናችሁን የሚገልጽ መረጃ ካደራጃችሁ አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ አለባችሁ።
- በሥራ ኢንተርፕራይዝ የተደራጃችሁ ከምታመርቱት ምርት ውጪ ባለ ዘርፍ እና ሰነድ ላይ እንደማንኛውም ተጫራች ድርጅት cpo ማስያዝ ይኖርባችኋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫትን አካተው ዋናውንና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ11ኛው የሥራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ይከፈታል።
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታ ራሱን ማግለል አይቻልም።
- የተጫራቾችን አድራሻ የሚገልጽ ሙሉ መረጃ ከሰነዱ ጋር መያያዝ አለበት።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ዕቃ ከጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ የተረጋገጠ /cpo/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የቢሮ መስተንግዶ ላይ የምትወዳደሩ የውሃና የቆሎ ሳምፕል ማቅረብ አለባችሁ።
- ሳምፕል ያላቀረበ ተጫራች ድርጅት ከጨረታ ውጪ ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራች ድርጅት የአሸነፋችሁትን ዕቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት በማጓጓዝ ማቅረብ አለባችሁ።
- አድራሻ፡- ከመድኃኒዓለም ት/ቤት ወደ አበበ ቢቂላ ስታዲየም መውረጃ 300 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-8-27-81-54/
- ማሳሰቢያ፡- በተጫረታችሁት ዕቃ ላይ ዋጋ ስታስገቡ ቫትን ያካተተ መሆን ይጠበቅበታል።
- መወዳደር የሚቻለው ንግድ ፈቃዱ ላይ በተሰጠው ስራ ዘርፍ ብቻ ነው።
- ተጫራቾች ያስገባችሁትን ሳምፕል በቂ ማስቀመጫ ቦታ ስለሌለን አሸናፊና ተሸናፊ ከተለየ በኋላ በ60 /ስልሳ የሥራ ቀናት ውስጥ እንድትወስዱ እያሳሰብን በተቀመጡት ቀናቶች ውስጥ የማይወስድ ተጫራች ድርጅት ጽ/ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዛችሁትን cpo ለውል ማስከበሪያ /ማዞር/ ማስያዝ አይቻልም።
- ተጫራቾች ዋና የጨረታ ሰነድ ላይ ክፍል 2 እና ክፍል 6 በተጫራቾች የሚሞላውን ቅጽ መሙላት እና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅታችሁን ማህተም በማድረግ የጨረታ ሰነዱን መመለስ ይኖርባችኋል። ነገር ግን ክፍል 2 እና ከፍል 6 ላይ በተጫራቾች የሚሞላውን ቅፅ ያልሞላ ተጫራች እና የጨረታ ሰነዱን ካልመለሰ ተመላሽ ካላደረገ/ ከላይ የተጠቀሱትን ያላሟላ ተጫራች ጨረታው ውድቅ ይሆንበታል።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያም ሆነ በውል ማስከበሪያ የምታስይዙት በCPO ብቻ ነዉ። ከሲፒዮ ውጪ በቼክና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አይቻልም። ካስያዛችሁም ከውድድር ውጪ ትሆናላችሁ።
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 5 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት
