Tender Detail

Tender Details


የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር ጽ/ቤት ለ2018 የበጀት ዓመት የተለያዩ ዕቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 አስተዳደር /ቤት 2018 የበጀት ዓመት ቁጥር 002/2018 . በወረዳው አስተዳደር ስር ላሉ 18 /ቤቶች 1. የሠራተኞች የደንብ ልብስ 2. ስቴሽነሪ ዕቃዎች3. የጽዳት ዕቃዎች 4. አላቂ የቢሮ እቃዎች 5. የህትመት ውጤቶች 6. ቋሚ እቃዎች 7. የሰራተኛ ምገባ ምግብ የሚያዘጋጅ /የሚያቀርብ 8. ኩኪስ/ድፎ ዳቦ /ጠርሙስ ለስላሳ / 9. የሞንታርቦ 10የዲኮር ስራ 11የድንኳን ኪራይ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት በጨረታ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዙትን ሕጋዊ ሰነዶችን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።

የዘሙኑ ግብር የከፈሉ እና የቫት ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

ተጫራቾች በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሚጫረቱበት በየሎቱ ጠቅላላ ዋጋ 15000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፋባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፓርት ቦታው ድረስ ማቅረብ (ማስገባት) ይኖርባቸዋል።

ተጫራቾች የሚወዳደሩበት ዋጋ በታሸገ ፖስታ ውስጥ በመሙላት ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል። (ሲፒኦ ኮፒ ውስጥ ይግባ)

ተጫራቾች የአንድ ዋጋ ቫትን ጨምሮ ወይም ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይሞላ።

ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው እቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

የጨረታው ሰነድ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሰነድ የመግዣ ዋጋ የማይመለስ 500 /አምስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል በወረዳው ፋይናንስ /ቤት 3 ፎቅ ላይ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 230 እስከ 1130 ሰዓት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ የሞሉትን ዋጋ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው 7 የሥራ ቀናት ውል በመግባት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃውን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

 ጨረታው 11ኛው ቀን ጠዋት 400 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ታሽጎ ከጠዋቱ 430 ሰዓት በወረዳ 05 ፋይናንስ /ቤት የሚከፈት ይሆናል። ሆኖም ጨረታው የሚከፈተው የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

መሥሪያ ቤታችን የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 416 5909/ 011 470 3280 በመደወል ማግኘት ይቻላል።

አድራሻ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ቄራ ቀስተ ዳመና ስፖንጅ ፋብሪካ ማደያ አጠገብ።

በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተወዳዳሪዎች ከሆኑ አምራች ለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።

ለሚያቀርቡት እቃዎች በሙሉ ተወዳዳሪ ነጋዴዎች የጥራት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የወረዳ 05 ፋይናንስ /ቤት

Save Tender