አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ተያያዥ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር AMFI 02/2018
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ለተቋሙ አገልግሎት የሚውሉ የጽሕፈት መሣሪያዎች እና ተያያዥ የቢሮ እቃዎች በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ፡-
- ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት እና የአቅራቢነት ምዝገባ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚቀርብ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ወይም ጥሬ ገንዘብ በተከፈለበት በአኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ደረሠኝ ወይም የባንክ ዋስትና እንደምርጫቸው በአንዱ ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አሥር) ቀናት ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 (አሥራ እንድ ሰዓት) ድረስ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ በእሐዱ ባንክ ሒሳብ ቁጥር 0003230410101 ገቢ በማድረግ ገቢ የተደረገበትን ደረሰኝ አቅርበው ከአኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ወሰን ቅርንጫፍ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሣባቸውን የያዙ ሰነዶች የዋጋ ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው በሰም በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 11ኛው ቀን ሲሆን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ብቻ ከአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ኢማ ወሰን ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ታሽጎ በዚያው እለት ከቀኑ 5፡00 (አምስት ሰዓት) ላይ በግልጽ ተከፍቶ የእቃው ዋጋ ተጫራቾችና ታዛቢዎች ባሉበት ይነበባል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም ብሔራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት ይከፈታል፡፡ ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች በጨረታ ሰነዱ በተቀመጠው አግባብ በራሳቸው ሙሉ ወጪ አኩፋዳ ማይከሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና መ/ቤት (ደብረ ብርሃን እጼ ዘርዓ ያእቆብ ሕንጻ) ድረስ አምጥተው ገቢ ማድረግ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በተቋሙ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳና በደብዳቤ እንገልፃለን፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 637 66 68 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
