በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት በመደበኛ ግልጽ ጨረታ ቁጥር 002/2018 ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች መስፈርቱን ከሚያሟሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅቶች ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።
- ሎት 1 - አላቂ የቢሮ እቃዎች ግዥ
- ሎት 2 - የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
- ሎት 3 - የህትመት ውጤቶች ግዥ፣
- ሎት 4 - የሥራና ደንብ ልብስ እና ተዛማች እቃዎች ግዥ
- ሎት 5 - ልዩ ልዩ የአይን መነጽር ግዥ
- ሎት 6 - የአይቲ /የመረጃ ቴክኖሎጂ/ እቃዎች ግዥ
- ሎት 7 - የተሽከርካሪዎች መለዋወጫ እቃዎች ግዥ
- ሎት 8 - ምንጣፍና መጋረጃ ግዥ እና ከነ አክሰሰሪው እቃዎች ጋርና ከነእጅ ዋጋው
- ሎት 9 - የህንፃ መሳሪያዎች እና ኤሌክትሪክ እቃዎች ግዥ
- ሎት 10 - የፕሪንተር፣ ፎቶ ኮፒና ተዛማጅ እቃዎች ጥገና እና ሰርቪስ
- ሎት 11 - የታሸገ ውሃ ግዥ
- ሎት 12 - የገብስ ቆሎ የኦቾሎኒ እና ሽንብራ ድብልቅ
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች በገንዘብ ሚኒስቴር በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝርና በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በጨረታ መሳተፍ የሚችሉ ለመሆናቸው ከሚመለከተው ግብር ሰብሳቢ መ/ቤት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉና በዳግም ምዝገባ የተመዘገቡ ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በጨረታ ሰነዱ ላይ በየሎቶቹ ለጨረታ ማስከበሪያ የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በመመልከት በምትወዳደሩበት ሎት የተቀመጠውን ገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክፍለ ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት ስም በማስያዝ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባችሁ፣
- ተጫራቾች የሚጫረቱባቸውን እቃዎች ዓይነት ለመለየት የሚያስችል እቃዎች ስፔስፍኬሽን ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ ቢቀርብ ይመረጣል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ታክስን ያካተተ መሆን አለበት፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ሰነድ በአንድ ኢንቨሎፕ ሲሆን በአንደኛው ኢንቨሎፕ ፋይናንሺያልና ቴክኒካል መግለጫ ኦርጅናልና ኮፒው በዝርዝር ተሞልቶ እንዲቀርብና ኦርጅናልና ኮፒውን ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ድረስ 5ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 502 ለዚሁ ጨረታ ሲባል በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- የጨረታው ሳጥን ማስታወቂያ በወጣ በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4:00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 ይከፈታል፣
- የተጠቀሰው ቀን በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፣
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ክፍያ በመፈፀም የጨረታ ሰነዱን 5ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 502 መውሰድ ይችላሉ፣
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ቅ/ጽ/ቤቱ መጋዘን ወይም ስቶር ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፣
- ቅርንጫፍ /ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፣
አድራሻ፡-
መገናኛ ከ22 ታክሲ መያዣ ዝቅ ብሎ አማረ አብርሃምና ቤተሰቦቹ ህንፃ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502 ነው። ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ የስልክ ቁጥር 011 668 42 07 ደውላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የየካ ክ/ከተማ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅ/ጽ/ቤት
