Tender Detail

Tender Details


የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚከተሉት የግዥ አይነቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የሚከተሉት የግዥ አይነቶች መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት 1 የገበያ ትንበያ ጥናት ለማስጠናት የአገልግሎት ግዥ

ሎት 2 እስቴሽነሪዎች

ሎት 3 የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሶች

ሎት 4 የጽዳት እቃዎች

ሎት 5 የተሽከርካሪ ጌጣጌጦች

ሎት 6 የፕሪንተር እና ፎቶ ኮፒ ቀለም

ሎት 7 የደንብ ልብስ

ሎት 8 የተለያዩ ህትመት

ሎት 9 የተለያዩ አገልገሎት ግዥዎች

ሎት 10 የመኪና ጎማዎች

ሎት 11 የተለያዩ ፈርኒቸሮች

ሎት 12 መጋረጃ

ሎት 13 ምንጣፍ

1. በዘርፍ ህጋዊ ፍቃድ ያለውና 2017 . የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸው::

2.ለእቃ አቅራቢነት ስለመመዝገባቸው እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታከስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው መረጃ ማቅረብ የሚችሉ

3. የጨረታ ማስከበሪያ ብር ለእያንዳንዱ ሎት 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) ወይም በባንከ የተረጋገጠ የከፍያ ማዘዣ በአዲስ አበባ ከተማ አሰተዳደር ንግድ ቢሮ ስም CPO (ጋራንትድ ቦንድ) በማሰራት ማስያዝ የሚችሉ ::

4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ ከመጨረሻው ቀን በኋላ ለተጨማሪ 90 ቀናት ፀንቶ ይቆያል::

5. ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ıo ተከታታይ የስራ ቀናት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነዱን

መግዛት ይችላሉ፡፡

6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን የአንዱ ዋጋ እና ጠቅላላ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታከስን ያካተተ ዋጋ ስርዝ ድልዝ ሳይኖረው ቢሮው በሰጣችሁ ፎርማት ላይ በመሙላት እና የድርጅታችሁ ማህተም ፊርማና ሙሉ አድራሻችሁን በመግለጽ

6.1 ፋይናንሽያል አንድ ኦርጅናል እና ፋይናንሽያል አንድ ኮፒ

6.2 ቴክኒካል እንድ ኦርጅናል እና ቴክኒካል አንድ ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ በተለያዩ ፖስታዎች ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

6.3 ከሎት 1 ከሎት 3 ከሎት 9 ከሎት 10 ከሎት ውጪ ያሉትን ሎቶች ናሙና (sample) ማቅረብ ግዴታ አለባችሁ:: ናሙና (sample) ያላቀረበ ድርጅቶች ከውድድሩ ውድቅ ይደረጋል::

7. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከሰኞ - ዓርብ 230 – 1100 ሰዓት ድረስ የግዥ ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 803 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡

8. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ11ኛው ቀን ማለትም የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

9. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ተጫራቾች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት (ማቅረብ) አይቻልም

10. ቢሮው ብዛቱን በተመለከተ በጨረታ ሰነዱ ላይ በገለፅነው መሰረት መቀነስና መጨመር የሚችል መሆኑን እንገልፃለን፣

11. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0111703024/በመደወል መረጃ መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻ - በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ውቤ በረሃ

8 ፎቅ ቢሮ ቁጥር 803

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ

Save Tender