ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 008/2018 ዓ.ም
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን መስፈርቱን የሚያሟሉ ብቁ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
· ሎት 1 የተቃጠለ ዘይት፤
· ሎት 2 ያገለገሉ የክር ጎማዎች 12*20፣ ያገለገሉ የሽቦ ጎማዎች 12*20፣ ያገለገሉ ቲዩብለስ ጎማዎች፤
· ሎት 3 ያገለገሉ የተለያዩ ፊልትሮዎች፤
· ሎት 4 ያገለገሉ የመኪና ባትሪ 60 AM፣ ባትሪ 75 AM፣ ባትሪ 90 AM፣ ባትሪ 150/155 AM፣ ባትሪ 200 AM፤
· ሎት 5 ያገለገሉ በርሜሎች (ግማሽ)፣ ያገለገሉ በርሜሎች (ሙሉ)፤
· ሎት 6 ያገለገሉ ቆርቆሮዎች (ሙሉ)፣ ያገለገሉ ቆርቆሮዎች (ግማሽ)፤
· ሎት 7 ያገለገሉ ጠረጴዛዎች፤
· ሎት 8 ያገለገሉ የተለያዩ ወንበሮች፤
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ለእያንዳንዱ ሎት ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት በዘርፉ አግባብነት ያለው የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ኮፒ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ከሎት 1 እስከ ሎት 8 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
4. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ 20,000.00 (ሃያ ሺህ) ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
5. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
6. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የፐብሊከ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፡- ስልክ፡- 011-5-50-45-64
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
