በለሚኩራ ክ/ከተማ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ጥቅል ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቶ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በለሚኩራ ክ/ከተማ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የ2ኛ ዙር ጥቅል ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አውጥቶ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02/2018
|
|
የዕቃ ዝርዝር |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ |
|
ሎት 1 |
አላቂ የትምህርት ዕቃ |
24,000 |
|
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ እቃ |
20,000 |
|
ሎት 3 |
የፅዳት ዕቃ |
20,000 |
|
ሎት 4 |
ለህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች መግዣ |
22,500 |
|
ሎት 5 |
የደንብ ልብስ |
8,000 |
|
ሎት 6 |
ለአላቂ የህክምና እቃ |
2,000 |
|
ሎት 7 |
ህትመት |
3,000 |
|
ሎት 8 |
ፐላንትና ማሽነሪ መግዣ |
48,000 |
|
ሎት 9 |
ልዩ ልዩ መሳሪያዎች እና መፃህፎች |
1,150 |
|
ሎት 10 |
ለምርምር እና ለልማት አላቂ እቃዎች |
8,000 |
ስለሆነም መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቶች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ህጋዊ ፍቃድ ያላቸዉና የዘመነ ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 4 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከዋጋ ማቅረቢያ ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ከላይ የተዘረዘሩት እቃዎች ለእያንዳንዳቸው የዋጋ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 ድረስ በመቅረብ መግዛትና መጫረት ይችላሉ፡፡
8. ተጫራቾች ዋጋ የሞሉበትን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየትና በ 2 ፖስታ በማሸግ እንዲሁም የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 10ኛው የስራ ቀን ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 የሚከፈት ይሆናል፤
9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በር/መምህርት ቢሮ ይከፈታል፡፡
10. ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በቀኑ ባይገኙም ጨረታው የሚከፈት ይሆናል።
11. በጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከት/ቤቱ ጋር የግዥ ውል ስምምነት መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ዕቃ ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
13. አሸናፊ ድርጅቶች ያሸነፋዋቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወደ መስሪያ ቤቱ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ቅሬታ ካላቸው የጨረታው አሸናፊው ከተለየበት ቀን ጀምሮ በ7 የሥራ ቀናት ውስጥ ቅሬታቸውን ለጨረታ ኮሚቴ በጽሁፍ ማቅረብ አለባቸው፡፡
15. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች አሟልተው የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፋይናንስና ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 5 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
16. ሁለት ተወዳዳሪዎች ለአንድ ዕቃ ተመሳሳይ ዋጋ ቢያቀርቡ ኮሚቴው በጥራት ወይም ሌላ የቴክኒከ መስፈርት በመጠቀም አሸናፊ ይለያል፡፡
17. ሁሉንም መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች በዋጋ ወይም በጥራት አሸናፊው የሚለይ ይሆናል፡፡
18. መ/ቤቱ አሸናፊውን ተጫራች በሚመርጥበት ጊዜ የሚገዛውን ዕቃ ወይም አገልግሎት ብዛት ወይም መጠን እንደ አስፈላጊነቱ እስከ 20% ለመቀነስ ወይም ለመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
19. አሸናፊው ድርጅት የግዥ መጠየቂያ ወይም (Purchese Order) ከደረሳቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ማቅረብ የሚችሉና የሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች እስቶክ ላይ ያሉ መሆን አለባቸው፡፡
20. አነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት መጫረት የምትችሉት የንግድ ፍቃዳችሁን ኮፒ በማድረግ ይዛችሁ ማምጣት ስትችሉ ነው፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በግዥ አፈፃጸም መመሪያ ላይ ለአነስተኛና ጥቃቅን ተቋማት ባወጣው መመሪያ መሰረት ነው፡፡)
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 68 29 02 /0116 67 91 63 ወይም በአካል በሻሌ ለጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሰሚት ሳፋሪ ቦሌ ምድብ ችሎት ፍርድ ቤት አጠገብ ፋይናንስ ቡድን መሪ ቢሮ በመቅረብ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በለሚኩራ ክ/ከተማ የበሻሌ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
