Tender Detail

Tender Details


የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፤ የኤሌክትሪከ ዕቃዎች : የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተ


የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር -26/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ //ቤት የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን //ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት የተለያዩ ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፤ የኤሌክትሪከ ዕቃዎች : የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ፅታዎች እና ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች(ግለሰብም ሆነ ድርጅት) ለጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደስ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ፣የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

2 ማንኛዉም ተጫራች የጨረታዉን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 200 እስከ 600 ከሰዓት 700 እስከ 11 00 ሰዓት፣ ቅዳሜ 200 እስከ-600 ሰዓት ድረስ በቅ//ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደርቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100( አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላከሎት ማድረግ ይቻላል።

3. ያገለገሉ ተሸከርካሪዎች እና ያገለገሉ ሞተርሳይከሎች ላይ መወዳደር የሚፈልግ ተጫራች ማንኛዉም እድሜዉ 18 አመት በላይ የሆነ ኢትዮጲያዊ መወዳደር ይችላል።

4. ተጫራቾች ለጨረታዉ ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ //ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላለ ዋጋ 5%(አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን C.P.O በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።በተጨማሪ ሀራጅ ጨረታ ለሚሳተፉ ተጫራቾች ለመገናኛ ዕቃዎች ለመዋቢያና የንጽህና መጠበቂያ ዕቃዎች አልባሳትና ጨርቃ ጨርቅ እና ለሞተር ሳይከል ለእያንዳንዱ ኮድ ብር 50,000( ሀምሳ ሺህ) ለተሸከርካሪዎች ለእያንዳንዳቸው ብር 1,000,000(አንድ ሚልዮን ብር) የጨረታ ዋስትና ( C.P.O) ለእያንዳንዱ የጨረታ ኮድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

5 ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛዉ) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን 6ኛው (በስድስተኛዉ) ቀን ጠዋት 400 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 405 ፔፕሲ ፋብሪካ ፊት ለፊት በሚገኘው የሐዋሳ ///ቤት አዲሱ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ጨረታው የሚጀምርሲሆን ግልፅ ጨረታ ከተጠናቀቀ በኋላ የሀራጅ ጨረታው ይጀመራል። ነገር ግን ጨረታው በበዓል እና እሑድ ቀን የሚውል ከሆነ የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታ ይሆናል።

6 ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸዉን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበዉ ቅጽ ላይተጫራቹ ያተረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ከፍት ቦታ ከነ ቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልከ በመሙላት ኢንቨሎፕ ወይም ፖስታ ማቅረብ አለባቸዉ። ከዚህ ሰነድ ውጭበሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ // ቤቱ ለመቀበል አይገደድም።

7- ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃ አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም በተጨማሪ ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠዉን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም።

8 ማንኛዉም ተጫራች የሰጠዉ የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆቅ//ቤቱ የጨረታዉን ዉጤት እስከሚያሳዉቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

9 ማንኛዉም ተጫራች ጨረታዉ ከተከፈት በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም። በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡

10.ተጫራቾች የዕቃዉን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ//ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም።

11.ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው።

12. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5(አምስት) የስራ ቀናት ዉስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፤ ይህንን ባያደርጉ ጨረታዉ ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ//ቤቱ ገቢ በማድረግ ፅቃው ድጋሜ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል።

13. //ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 046-212-53-96/ 046-212-65-95

የሐዋሳ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender