የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት በ12 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር አ/አ/ከ/አ/ለ/ሴ/ተ/ክ/ማ/ማ (02/001-012/2018)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2018 በጀት ዓመት በ12 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት ቁጥር |
የሚገዛው እቃ/አገልግሎት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ ግዥ |
30,000.00 сро |
|
ሎት 2 |
አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዥ |
20,000.00 сро |
|
ሎት 3 |
የህትመት ግዥ |
10,000.00 сро |
|
ሎት 4 |
አላቂ የህክምና ዕቃዎች ግዥ |
50,000.00 сро |
|
ሎት 5 |
አላቂ የትምህርት ዕቃዎች ግዥ |
50,000.00 сро |
|
ሎት 6 |
ሌሎት አላቂ ዕቃዎች ግዥ |
20,000.00 сро |
|
ሎት 7 |
የተለያዩ መሳሪያና መጻህፍት ግዥ |
10,000.00 сро |
|
ሎት 8 |
ለግብርና፣ ለደን ግብዓቶች ግዥ |
10,000.00 сро |
|
ሎት 9 |
ለመስተንግዶ ግዥ |
10,000.00 сро |
|
ሎት 10 |
ለተሸከርካሪዎችና ሌሎች ዕድሳት ግዥ |
10,000.00 сро |
|
ሎት 11 |
ለህንጻ፣ ለቁሳቁስና ለተገጣጣምዎች ዕድሳትና ጥገና |
30,000 сро |
|
ሎት 12 |
ለፕላንት፣ ለማሽነሪና መሳሪያ ግዥ |
100,000 сро |
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የግዥና ፋይናንስ መመሪያዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መኖራቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ።
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
5. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ተጫራቾች ከተደራጁበት ክፍለ ከተማ ወይም ወረዳ በመስሪያ ቤቱ የፅህፈት ቤት ኃላፊ ስም የተፈረመ ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ እና አምራች መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
6. ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአካውንት ቁጥር 1000640967181 በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት እሰከ 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ከማዕከሉ ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በስፔስፊክሽኑ መሰረት ብቻ በማድረግ ቫትን ጨምረው ሞልተው በሰም አሽገው ኤንቨሎፕ ላይ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው በመለየት የግዥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሰረት ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
8. ተጫራቾች ሌሎች መረጃዎችን ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
9. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ናሙና ለተጠየቀባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
11. የጨረታ ማስከበሪያ በcpo ነው።
ማሳሰቢያ፡- የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 11ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው አካላት በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጀርባ 500 ሜትር ገባ ብሎ ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶ እና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል 1ኛ ፎቅ የግዥ፣ ንብረትና ህንፃ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ
ስልክ ቁጥር፡- 0114378666
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል
