Tender Detail

Tender Details


መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የሰነድ ቁጥር 121

 

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። ቁሳቁሶቹም፡

1.     አሉሚኒየምና አሉሚኒየም ቁሳቁሶችና ቶቦላሬዎች (በድጋሚ የወጣ)

2.     ብዛት ያላቸው ያገለገሉና ለመለዋወጫ ብቻ የሚያገለግሉ ሞተር ሳይሎች፣

3.     የኤሌትሮኒ ዕቃዎች (ኮምፒዩተር፣ ፕሪንተር፣ ላፕ ቶፕ፣ ቶነር፣ ፍሪጅ፣ የውሃ ማጣሪያ ወዘተ)

4.     አውቶ ሌቭ (አሮጌና የማይሠራ ለመለዋወጫ ብቻ የሚያገለግል)

5.     የተነቃቀሉ ጣውላዎች፤

6.     በሸራና በብረት የተሠሩ ወንበሮች

7.     የተቃጠለ ዘይት በበርሜል፤ የመኪና መለዋወጫዎች እና የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፤ ለሚኩራ ፍለ ከተማ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፤ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተርስቲያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመወሰን እና በመሙላት ካሸጉ በኋላ ሊገዙ የወሰኑበትን ዋጋ 10 በመቶ በማስላት የሚገኘውን ውጤት ለጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ በማሠራት ካዘጋጁ በኋላ በማኅበሩ የጠቅላላ አገልግሎት ፍል ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀን አየር ላይ ቆይቶ 11ኛው ቀን 430 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 500 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ የጨረታ ሣጥኑ በዕለቱ ልክ 700 ሰዓት ተዘግቶ 730 ሰዓት ተጫራቾችና ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ተጫራቾች መረጃ ከፈ በስልክ ቁጥር 0930 79-64-13 ወይንም 0975-26-41-59 ደው መጠየቅ ይችላሉ

 

የመቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማኅበር

Save Tender