Tender Detail

Tender Details


የንጋት ኮከብ ቅደመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የጽዳት ዕቃ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና፣ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የተለያዩ የጥገና ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የንጋት ኮከብ ቅደመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት የጽዳት ዕቃ፣ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎችና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች፣ የደንብ ልብስ፣ የተለያዩ የጥገና ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን፣ ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ለግዥ የቀረቡ ዕቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO በየሎቱ ቀርበዋል፤

·        ሎት 1- አላቂ የፅህፈት መሳሪያዎች እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች CPO ብር 6,100.00

·        ሎት 2- አላቂ የፅዳት እቃዎች CPO ብር 13,000.00

·        ሎት 3- የጥገና እቃዎች CPO ብር 7,900.00

·        ሎት 4- የደንብ ልብስ CPO ብር 3,600.00

·        ሎት 5- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች ብር 12,000.00

·        ሎት 6- ኤሌክትሮኒክስ ብር 9,000.00

ተጫራቾች ለምትወዳደሩበት ሎት የተጠቀሰውን ገንዘብ መጠን ማስያዝ የሚገባችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።

·        ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት የምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

·        የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

·        አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀበት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል መፈፀምና 10% የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

·        ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ክፍል የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

·        ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው። ተጫራቾች በተመረጠው ናሙና መሰረት 7 ቀናት ውስጥ እቃዎችን ለት/ቤቱ ንብረት ፍል ማስረከብ ይኖርባቸዋል።

·        ጨረታው የሚከፈተው አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ 11ኛው ቀን 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን 430 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

·        ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም።

·        መስሪያ ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

·        የጨረታ ማስከበሪያው በየሎቱ ይሆናል።

·        በጥቃቅን እና አነስተኛ ሥር ተደራጅቶ ለሚመጡ ተጫራቾች አምራች በሆኑበት ዕቃ ላይ ብቻ የሚወዳደሩ መሆን አለባቸው።

·        ማሳሰቢያ፡- ጨረታ ሰነዱ ሲገባ በሶስት ፖስታዎች የሚገባ ሲሆን አንደኛው ፖስታ ቴክኒካል ኦርጅናል ሁለተኛው ፖስታ ፋይናንሻል ኦርጅናል፤ ሶስተኛው ፖስታ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ኮፒ በማድረግ 3 ፖስታ ሆኖ መቅረብ አለበት።

አድራሻ፡- የካ/// ወረዳ 06 ከአቧሬ አደባባይ 100 ሜትር ገባ ብሎ ጀርመን /ቤት አጠገብ አቧሬ ጤና ጣቢያ ፊት ለፊት።

 

ስልክ ቁጥር:- 0115 578300/0921722704/0911918737

 

የንጋት ኮከብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ /ቤት

 

Save Tender