Tender Detail

Tender Details


የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በየሎቱ ተዘርዝረው የተገለጹትን የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 4/2018

 

የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በየሎቱ ተዘርዝረው የተገለጹትን፡-

·        ሎት-1 ለምግብ ማደራጃ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች ግዢ፣

·        ሎት-2 የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዢ፣

·        ሎት-3 water pump እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች ግዢ፣

·        ሎት-4 የምግብ ግብአት ግዢ፣

·        ሎት-5 የድንገተኛ እሳት ማጥፊያ መሙላት አገልግሎት ግዢ፣

·        ሎት-6 የፅዳት እቃዎች ግዢ፣

·        ሎት-7 የደንብ ልብስ ግዢ፣

·        ሎት-8 የፅዳት አገልግሎት አውት ሶርስ ግዢ፣

·        ሎት-9 የላውንደሪ አገልግሎት አውት ሶርስ ግዢ፣

የተለያዩ ግዢዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን የተጫራቾች መመሪያ ማክበር አስባቸው፡-

1.     ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN/ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማስረጃ እና ከገቢዎች የታደሰ የመጫረቻ ፈቃድ ደብዳቤ የሚያቀርቡ ሆኖ ሁሉንም የተጠየቁ ማስረጃዎች በግልጽ የሚታይና የሚነበብ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

2.     ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ዝርዝር የሚያሳይ ሰነድ በማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ጨረታው በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ቅዳሜ፣ ዕሁድ የበዓል ቀናትን ሳይጨምር በሚቆጠር እስከ 10ኛው ቀን 1045 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በሆስፒታሉ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

3.     ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ፖስታዎቹ ላይ ከውጭ ሎቶቹን በመፃፍና ማህተም በማድረግ፤ በየሎቱ ለየብቻ ተለይተው ፋይናንሺያል እና ቴክኒካል ኦርጂናል የማይመለስ ኮፒውን በመለየት የሚቀርብ ሆኖ ጨረታው በሚከፈትበት እለት ወይም እስከ 11ኛው ቀን 400 ድረስ ግዢ ክፍል በሚገኘው የጨረታ ቡድኑ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

4.     11ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ላይ የጨረታ ሳጥኑ ተዘግቶ (በዚሁ ዕለት) 11ኛው ቀን ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ቡድኑ ይከፈታል፡፡

5.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ ሳምፕል፤ ካታሎግ ይቅረብ በተባለው ላይ ያቀርባሉ፤ ስፔስፊኬሽን ያላቸውን በጥንቃቄ በማየት መጫረት ይኖርባቸዋል፡፡

6.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከሎት-1 እስከ ሎት-9 ለእያንዳንዱ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ የዋስትና ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

7.     ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

8.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነድ ላይ በተቀመጠው ሰነድ መሰረት ዋጋ ሲሞሉ ከቫት ጋር መሆኑን እና አለመሆኑን በማያሻማ ሁኔታ በግልጽ በመለየት በሆስፒታሉ የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

9.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዱ ላይ የማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ሃሳብ ካላቸው ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሆስፒታሉ የግዢና እቅድ ዝግጅት ዳይሬክቶሬት የሥራ ክፍል በጽሑፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

10. የጨረታ ማስከበሪያው አሸናፊዎች ተለይተው ውል እስኪፈጸም ድረስ እንደተያዘ ይቆያል፡፡

11. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባለው የቅሬታ ማቅረቢያ የሚታይበትን ቀን ጨምሮ 7 ቀን በኋላ አሸናፊዎች አዋርድ ወስደው 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) በዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ስም የተዘጋጀ በማስያዝ 3 ቀን ውስጥ ውል ተዋውለው በጨረታ ያሸነፉባቸውን እቃዎች ስፔስፊኬሽኑ እና ሳምፕል የቀረበባቸውን በሳምፕሉ መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

12. የጨረታ ሳጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚደርስ ሰነድ ሳይከፈት ለተጫራቹ ይመለሳል፡፡

13. የጨረታውን 20% መጨመርና 20% መቀነስ ይቻላል፡፡

14. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ላይ መሳተፍ የሚችለው በተሰማራበት የሥራ ዘርፍ ብቻ ሲሆን በአነስተኛና ጥቃቅን ንግድ ሥራ ዘርፍ የተሰማራችሁ የንግድ ሥራ መለያ ኮድ በደብዳቤ ላይ በመግለጽ ጨረታውን መሳተፍ የሚችሉ ይሆናል፡፡

15. ሆስፒታሉ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-515 -02- 42 በመደወል መረዳት

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል ቂርቆስ /ከተማ ፍል ውሃ አጠገብ ገባ ብሎ ይገኛል፡፡

 

በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር ጤና ቢሮ የዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል

Save Tender