የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ሃብት ማመንጨት ኢንተርፕራይዝ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት የደንብ ልብስና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ሃብት ማመንጨት ኢንተርፕራይዝ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች በሎት የተጠቀሱትን የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ግብዓት የደንብ ልብስና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
· ሎት አንድ፡- ለእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ የሚውሉ ግብዓቶች (ፋጉሎ፣ ፍሩሽካ፣ ላየም ስቶን...)
· ሎት ሁለት፡- የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች
· ሎት ሦስት፡ - የደንብ ልብስ (የስራ ልብስ) ዕቃዎች
· ሎት አራት - የእንቁላል ጣይ ቄብ ዶሮዎች (የ 45 ቀን፣ የ 2 ወርና የ 3 ወር)
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ -
1. ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ ሆነው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣ የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን የሚያረጋግጥ ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሠጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት አንድ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)፣ ለሎት ሁለት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፣ ለሎት ሦስት ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) እና ለሎት አራት ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ሲፒኦ ብቻ በማሰራት ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሠዓት እስከ ቀኑ አስር ሠዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመከፈል ደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሣባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎኘ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በኢንተርፕራይዙ ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ በወጣ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ 4፡30 በግልፅ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት ወይም በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓትና ቦታ በግልፅ ይከፈታል፡፡ ትክክለኛው የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚገለፅ ይሆናል/
6. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
7. ኢንተርፕራይዙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን /+251925750633/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ መገዘዝ ንግድና የማማከር ስራዎች ኢንተርፕራይዝ
