Tender Detail

Tender Details


በኢትዮጰያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/201 ከቀነ ገደቡ በላይ በመጋዘን በመቆየታቸው ምክንያት እንዲሁም የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 9 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም PERFUFME: SOAP HARMONY SHITY WITH SCARF, SHOE BRAND, MEN TROUSER


የተተው ዕቃዎች ግልፅ ጨረ ቁጥር -24/2018 ጨረታ

 

በኢትዮጰያ ጉምሩ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ /ቤት አስመጪዎች በተሻሻለው የጉምሩክ አዋጅ ቁጥር 1160/201 ከቀነ ገደቡ በላይ በመጋዘን በመቆየታቸው ምክንያት እንዲሁም የተተው ወይም የተወረሱ ዕቃዎችን በእቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 ንቀጽ 9 መሠረት የተተው ንብረቶችን ማለትም PERFUFME: SOAP HARMONY SHITY WITH SCARF, SHOE BRAND, MEN TROUSER SUPER SOFT BLANKET, SOFA COVER, PRINTED CAP, PRINTED CALENDER, WIRE PROFESSIONAL HOTELP, SPECFIC TELEPHONE LADY OPEN SHOES UPPER MATERIAL IMITATION AND DFFERNTE SHOES ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

በዚህም መሠረት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጫረት የሚፈልጉና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

1.     ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት፣ ብዛት፣ የጨረታ ሠነድ እና መመሪያ መግለጫ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ዘወትር ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 600 ከሰዓት በኋላ ከቀነ 700 እስከ ቀነ 1030 እና ዓርብ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 500 ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 730 እስከ ቀኑ 1030 እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋት 200 እስከ ቀኑ 530 የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመፈል ከቅርንጫፍ /ቤቱ ገቢ ሂሳቦች ቡድን መውሰድ ይችላሉ፡፡

2.     ተጫራ በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃ ጋር በዘርፉ የፀና ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ለመሆኑ ብር ሰብሳቢ /ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው ሆኖም ግምታዊ ዋጋቸው ከብር 500,000.00 በታች የሆነ ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታከስ ምዝገባ ሠርተፍኬት ማቅረብ ሳያስፈልግ መወዳደር ይችላሉ፡፡

3.     ማንኛውም ተጫራች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን የሚጫረትበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% ለጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ጨረታ ከመከፈቱ በፊት በቅድሚያ ማስያዝ ማስከበሪያ ይኖርበታል ተጫራቾች የሚያስይዙት CPO በቅርጫፍ /ቤቱ ሥም ETHIOPIAN CUSTOMS COMMISSION MODJO BRANCH OFFICE በሚል ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከአዲስ አበባ አዳማ እና ሞጆ ቅርንጫፎች መዘጋጀት አለበት፡፡ ተሳታፊዎች ዋጋ መሙላት የሚችሉት በቅርንጫፍ /ቤቱ ተዘጋጅቶ ማህተም ያረፈበት ሠነድ ላይ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመግዛት የሚወዳደሩበትን ዕቃ ቀድሞ ማየት ያለባቸው ሲሆን ዕቃውን ሳያዩ ለሚሞሉት ዋጋ //ቤቱ ኃላፊነቱን አይወስድም፡፡ በጨረታ ተሽጦ የተወሰደ እቃ ተመላሽ አይደረግም፣ ለእቃውም የተከፈለ ገንዘብ አይመለስም፡፡

5.     የግል ጨረታ ተሳታፊ ተጫራ እያንዳንዱን ዕቃዎች ለመግዛት የሚያቀርቡት የመጫረቻ ዋጋ፣ የሞሉበት ሠነድ፣ በተራ ቁጥር 2 የተገለፁትን ማስረጃዎች ኮፒ እና ያቀረቡት የመጫረቻ ዋጋ 5% ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO በኤንቬሎፕ በማሸግ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 8 ተከታታይ ቀናት እስከ የመጨረሻው ቀን ጠዋት 445 ድረስ በቅርንጫፍ /ቤቱ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይቻላል፡፡ የጨረታ ሣጥኑ ከታሸገ በኋላ የሚመጡ የመጫረቻ ሰነዶች ተቀባይነት አይኖራቸውም።

6.     የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የወጣበት ቀንን ጨምሮ 8ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:45 ታሽጐ በዚሁ ዕለት ጠዋቱ 500 ላይ ተጫራቾቹ ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቅርንጫፍ /ቤቱ ለጨረታ በአዘጋጀው ቢሮ ውስጥ ይከፈታል፡፡

7.     ማንኛውም በግልጽ ጨረታ የሚሳተፍ ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ዋጋ መቀየር ወይንም የሌላ ተጫራቾችን ዋጋ ተንተርሶ ዋጋ አሻሽሎ ማቅረብ አይችልም፣ በጨረታ ሽያጭ ውድድር ላይ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፤ ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ /ቤቱ የጨረታውን ውጤት ጨረታው ከተከፈተ በኋላ እራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይቻልም እና የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ ቅርንጫፍ /ቤቱ እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡

8.     የግልጽ ጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ አለበት፡፡ 5 (አምስት) ቀናት ውስጥ ገንዘቡ ገቢ ካልተደረገ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባን በተረጋገጠ CPO ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል

9.     በተራ ቁጥር 8 በተቀመጠው ጊዜ ውስጥ የአሸነፉበትን ዕቃ ዋጋ ገቢ አድርጎ ዕቃውን ያላነሳ ያልተረከበ እንደሆነ ለሚቆይበት ለተጨማሪ ጊዜ የመጋዘን ኪራይ ይከፍላል፡፡ ሆኖም ዕቃው 2 (ሁለት) ወራት ውስጥ ካልወጣ እንደተተወ ተቆጥሮ በጨረታ ሽያጭ ይወገዳል፡፡

10. አሸናፊው ተጫራች ዕቃዎችን ለመረከብና ለማጓጓዝ የሚያስፈልጉ ወጪዎችን ሁሉ ራሱ ይሸፍናል፡፡

11. ቅርንጫፍ /ቤቱ ለጨረታ የአቀረበውን ዕቃ ብዛት ለመጨመርም ሆነ ለመቀነስ ሙሉ መብት አለው በጨረታ በጨረታ አሸናፊው የተወሰደ እቃ አይመለስም፡፡

12. ቅርንጫፍ /ቤቱ ዕቃዎቹን ለመሸጥ የተሻለ አማራጭ ወይም ዘዴ ከአገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 022-236-90-94 ላይ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በገቢዎች ሚኒስቴር ጉምሩክ ኮሚሽን የሞጆ ጉምሩክ ቅርንጫፍ /ቤት

 

Save Tender