የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽሕፈት ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር- አ/አ/ብ/ፖ/ቅ/ጽ-02/2018
የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽሕፈት ቤት ለጽ/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
· ሎት፡ 1 የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች
· ሎት፡ 2 አይሲቲ እቃዎች
· ሎት፡ 3 የዲኮር አገልግሎት
· ሎት፡ 4 የሳውንድ ሲስተም ኪራይ አገልግሎት
· ሎት: 5 የህትመት አገልግሎት
· ሎት፡ 6 የድንኳን ወንበር እና ጠረጴዛ ኪራይ አገልግሎት
· ሎት: 7 የቧንቧ እቃዎች
· ሎት፡ 8 የኤሌክትሪክ እቃዎች
· ሎት፡ 9 የአዳራሽ ጥገና እና እድሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1.1 የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና በዘርፉ የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ
1.2 የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
1.3 የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው
1.4 የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ያላቸው
1.5 በግዥ ኤጀንሲ አቅራቢዎች ሊስት የተመዘገቡ እና ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
1.6 ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት ስለ ግብር አከፋፈል የሚገልጽ በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
1. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ 400.00 (አራት መቶ) ብር በመክፈል ትራፊክ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት ስድስተኛ /6/ ፎቅ ቢሮ ቁ 6-03 በግንባር በመቅረብ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሠረት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው አይነት |
የሲፒኦ መጠን |
የቆይታ ጊዜ |
|
1 |
የጽሕፈት መሳሪያ እቃዎች |
10,000 |
የ1 ጊዜ ግዥ |
|
2 |
አይሲቲ እቃዎች |
20,000 |
>> |
|
3 |
የዲኮር አገልግሎት |
50,000 |
ውል ታስሮ ለ1 ዓመት የሚቆይ |
|
4 |
የሳውንድ ሲስተም ኪራይ አገልግሎት |
50,000 |
ውል ታስሮ ለ1 ዓመት የሚቆይ |
|
5 |
የህትመት አገልግሎት |
50,000 |
ውል ታስሮ ለ1 ዓመት የሚቆይ |
|
6 |
የድንኳን ወንበር እና ጠረጴዛ ኪራይ አገልግሎት |
30,000 |
ውል ታስሮ ለ1 ዓመት የሚቆይ |
|
7 |
የቧንቧ እቃዎች |
10,000 |
የ1 ጊዜ ግዥ |
|
8 |
የኤሌክትሪክ እቃዎች |
10,000 |
የ1 ጊዜ ግዥ |
|
9 |
የአዳራሽ ጥገና እና እድሳት |
50,000 |
የ1 ጊዜ ግዥ |
3. ጨረታውን ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊ ድርጅቶች አሸናፊነታቸው እንደተረጋገጠ የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላው ዋጋ 10% ማስያዝ አለባቸው።
4. ተፈላጊውን የጥራት ደረጃ ያልጠበቀ ዕቃ ማቅረብ ከአቅራቢነት ያሰርዛል።
5. ስርዝ ድልዝ ያለው የጨረታ ሠነድ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት በመለየት ዋጋቸውን ጨረታ ሠነዱ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ላይ ብቻ ከቫት በፊት እና በኋላ ነጠላ ዋጋ በመሙላት እና አሪጅናል እና ኮፒውን በተለያየ ፖስታ እንዲሁም ቴክኒካል ሠነድ ከሲፒኦ ጋር ኦሪጅናል እና ኮፒውን ለብቻ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ በ1 ፖስታ ማሸግ ከጨረታ ውጪ ያደርጋል።
7. ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች በሙሉ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ናሙና ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የአይሲቲ እቃዎች ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ሠነዶቻቸውን በተለያየ ፖስታ በመለየት ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ከጨረታ ሠነዱ ውጪ ተሞልቶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
9. ጨረታው ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በአየር ላይ ከዋለ በዋላ በ11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ቀን 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጽ/ቤቱ 7ኛ ፎቅ በግልጽ ይከፈታል። የጨረታ መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
10. የጨረታ ሂደቱን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
11. አንዱ ድርጅት በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም፡፡
12. መ/ቤቱ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ
ስልክ ቁጥር: 011-6-67-44-30 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት
