የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር አ/አ/ከ/አ/የሰ/ፀ/አስ/ቢሮ እቃ/ግ/ጨ/005/2018 ዓ.ም.
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
· ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያዎች
· ሎት 2. የመኪና እቃዎች
· ሎት 3. ደንብ ልብስ
· ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ
· ሎት 5. የሻይ ቡና እቃዎች
· ሎት 6. ፈርኒቸር
ስለሆነም ጨረታውን መካፈል የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመሪያዎች በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው የዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ቲን እና (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ፒያሳ ከሚገኘው ከንቲባ ፅ/ቤት 2ኛ ፎቅ ከመ/ቤቱ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት መግዛት ይችላሉ ።
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሚወዳደሩበት ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ወይም የባንክ ዋስትና /unconditional/ በመ/ቤታችን ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ የኢንሹራንስ ዋስትና አንቀበልም።
· ሎት 1. የፅህፈት መሳሪያ--------------------------- 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)
· ሎት 2. የመኪና እቃዎች--------------------------- 5,000.00 (አምስት ሺ ብር)
· ሎት 3. ደንብ ልብስ------------------------------ 1,000.00 (አንድ ሺ ብር)
· ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ ዕቃ------------------------ 50,000.00 (ሃምሳ ሺ ብር)
· ሎት 5. የሻይ ቡና እቃዎች------------------------ 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)
· ሎት 6. ፈርኒቸር-------------------------------- 2,000.00 (ሁለት ሺ ብር)
4. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ሞልተው በመፈረም እና ህጋዊ ማህተም በማድረግ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ኦሪጅናል እና ኮፒ በየሎቱ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይበተራ ቁጥር 2 በተጠቀሰው አድራሻ የመ/ቤቱ ግዢ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ ከ11ኛው ቀን እስከ 3፡30 ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በመ/ቤቱ ዋጋ መሙያ ያልተሞላ ዋጋ ፊርማና ማህተም የሌለው የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት አይኖረውም።
5. ጨረታው በ11ኛው ቀን ጠዋት 3፡30 ላይ ታሽጎ በ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል። ናሙና የተጠየቀባቸው ዕቃዎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት የድርጅታቸውን ማህተም በማድረግ ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች በሚጫረቱበት እያንዳንዱ እቃ ጥራት በቴክኒክ ብቃታቸው ከተመረጡ በዋጋ የሚወዳደሩ ይሆናል፡፡ አማራጭ ጨረታ አይፈቀድም።
7. አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ጠቅላላ እቃዎች ዋጋ 10 በመቶ ውል ማስከበሪያ በማስያዝ አሸናፊነቱ ከታወቀበት ከ7ኛ ቀን ጀምሮ በ 7 ቀናት ውስጥ ውል መፈረም አለበት።
8. በተራ ቁጥር 7 መሰረት ውል የማይፈጽሙ አሸናፊዎች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ለመንግስት ገቢ በማድረግ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ መጠቀም ይችላል።
9. አሸናፊ የሆነ ድርጅት አሸናፊ የሆነባቸውን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ከንቲባ ፅ/ቤት ምድር ቤት ንብረት ክፍል ድረስ በማምጣት ለመ/ቤቱ ማስረከብ ይኖርበታል።
10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 11 57 54 39 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ- ፒያሳ ከንቲባ ፅ/ቤት ጊቢ ውስጥ 2ኛ ፎቅ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ
