Tender Detail

Tender Details


የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር - ኢፕድ 016/2108

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተገለጹትን ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት1. የተለያዩ ለህጻናት ማቆያ የሚያገለግሉ ዕቃዎች

ሎት2. ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ላፕቶፕ እና ሞባይል ቀፎ ግዥ)

ሎት3. የተፈጥሮ አበባ አቅርቦት (ንጥል አበባ በተለያየ ቀለም፣ በተለያየ ቀለም የተዘጋጀ የጠረጴዛ አበባ እና እስትሪፕ አበባ) አቅርቦት ለአንድ ዓመት በውል የሚሰራ

ሎት 4. ለካፍቴሪያ የሚሆኑ የፈርኒቸር እቃዎች

ስለሆነም፡- ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

1.     በሥራ ዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፣የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያገለግል ታክስ ክሊራንስና በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው።

2.     ዕጩ ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሎት በመፈል ግዥውን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ፋይናንስና ግዥ ዳት ግዥ ቡድንበአካል በመምጣት ይህ የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ 16 ተከታታይ ቀናት በመውሰድ የሚወዳደሩበትን ዝርዝር ዋጋ ከቫት ጋር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን 4 በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦሪጅናሉንና ኮፒዎቻቸውን ለየብቻ በማቅረብ ጉዳዩን አስመልክቶ በተዘጋጀው በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ግዥ ቡድን በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

3.     ዕጩ ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ የሚዉል ብር

ለሎት 1. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ለሎት 2. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ለሎት 3. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር)

ለሎት 4. ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ../ቢድ ቦንድ ማስያዝ አለባቸው።

4.     ጨረታው ዕጩ ተወዳዳሪዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው የሥራ ቀን የጨረታ ሳጥኑ በፋይናንስና ግዥ ዳይሬክቶሬት ከረፋዱ 400 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ 430 ሰዓት በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 1 ፎቅ በአቅርቦት መመሪያ ይከፈታል። ሆኖም ግን የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል

5.     /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ስልክ ቁጥር 011 1 56 98 69

ኢሜይል procurement@press.et

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም መተሚያ ድርጅት ፊትለፊት

 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት

Save Tender