መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ጊቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰነድ ቁጥር 122
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ጊቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉ ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ቁሳቁሶቹም፡
1. አውቶ ክሌቭ (አሮጌና የማይሰራ ለመለዋወጫ ብቻ የሚያገለግል)
1. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ፣
2. የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ጎማዎች ፤
3. የተነቃቀሉ ጣውላዎች፤
4. የብረት ሸልፍና ቁርጥራጭ ቆርቆሮዎች፤
5. በሸራና በብረት የተሰሩ ወንበሮች፤
6. አሮጌ ሻንጣዎች ናቸው።
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 400 (አራት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን ዕቃዎቹን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ በሰነዱ በእያንዳንዱ ቁጥር አንፃር የተለዩትን ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት እና ዕቃውን ለመግዛት ያስገቡትን ዋጋ 10% ለጨረታ ማስከበሪያ ከያዘ ሲ.ፒ.ኦ ጋር በማያያዝ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ15ው ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን እሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
የጨረታ ሣጥኑ በዕለቱ ልክ በ7፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ7፡30 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0930-79-64-13 ወይንም 0975-26-41-59 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር
