በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃ እና አገልግሎት፡- ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት2 የተሽከርካሪ ጎማ፣ ሎት3. የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 5. ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 03/2018
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ሸዋ ዞን የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለሴ/መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል እቃ እና አገልግሎት፡- ሎት 1 እስቴሽነሪ፣ ሎት2 የተሽከርካሪ ጎማ፣ ሎት3. የግንባታ እቃዎች፣ ሎት 4. ኤሌክትሮኒክስ እና ሎት 5. ደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ያላቸው።
4. የሚሞሉት ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተ.ቁ 1-4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር እያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
6. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ማግኘት ይቻላል፡፡
8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩበት ለእስቴሽነሪ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ብቻ፣ ለተሽከርካሪ ጎማ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ ፣ ለግንባታ እቃዎች 15,000 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ/፣ ለኤሌከትሮኒክስ 5,000 /አምስት ሺህ ብር/ ብቻ እና ለደንብ ልብስ 3,000 /ሶስት ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው።
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና /ኦሪጂናል እና ቅጂ /ኮፒ/ በማለት በጥንታቄ በታሸገ ፖስታ በግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 05/09/2018 ዓ.ም ጠዋት 4:00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሀላፊ ከፍል በቢሮ ቁጥር1 በ05/09/2018 ዓ.ም. ጠዋት 4:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቹ የዕቃውን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፍኬሽን/ በማሟላት ዕቃው የተመረተበትን ሀገር የአምራቹን ስም፣ የዕቃውን ሞዴልና የመሳሰሉትን አካቶ መሙላት ይጠበቅበታል፡፡
12. ውድድሩ በሎት ድምር ዋጋ ወይም በነጠላ ዋጋ ሊሆን ይችላል፡፡
13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 4 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0224720080 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
14. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ ሙበቱ የተጠበቀ ነው።
የበረኸት ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
