የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በድጋሚ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
መለያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/02/2026
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር DBE/NCB/CGPSD/01/2026 ዝግ ጨረታ አውጥቶ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በድጋሚ ግልጽ ጨረታ በሎት የተዘረዘሩትንና በባንኩ ካፒታል ዕቃዎች ግዥና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ሰነዳቸውን ማግኘት የሚቻል ሲሆን እነዚህን
- የጋርመንት ማሽኖች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ/ ኢንቨስትመንት ፈቃድ ያላቸው፣ የቀረጥ ነጻ ፈቃድ/መብት ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ጊዜው ያላለፈበት ፍቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚሳተፉበትን የጨረታ ሎት የመነሻ ዋጋውን ዋጋ 25% (ሀያ አምስት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ስም በጨረታው ዕለት ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 12 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በባንኩ 3ኛ ህንጻ 2ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል።
- አሸናፊው ያስያዘው ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ጋር ሲታሰብለት፣ ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
- የተዘረዘሩትን እቃዎች የጨረታው አሸናፊ እቃዎቹን እንዲያነሳ ከተነገረው በኋላ በአስር (10) የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ ገቢ በማድረግ እቃውን የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡ ይህ ካልሆነ ጨረታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል።
- ማሽነሪዎቹን መመልከት የሚፈልጉ ተጫራቾች ገላን ከተማ በሚገኘው የባንኩ መጋዘን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር ቅዳሜ ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት በአካል በመገኘት መመልከት ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት የካፒታል ዕቃዎች ግዢና አቅርቦት ዳይሬክቶሬት ስልክ ቁጥር፡ +251-11 524-4490 ወይም ኢ-ሜይል: cgpsd2026@dbe.com.et መጠየቅ ይችላሉ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
