Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Engineering Corporation (የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን)
  • Address ከመገናኛ አደባባይ ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚወስደው ዋና ቀለበት መንገድ ወደ አደይ አበባ ስታዲዬም (የኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል) የሚያስገባው መገንጠያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 118720722
  • Websitehttps://eec.com.et/
  • Deadline23 Jun 2026, 10:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • opening date2026-06-23 10:30:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Personal Protective Safety Equipment , Safety Clothe And Shoes

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሥራና የአደጋ መከላከያ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ../../08/2018

 

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የሥራና የአደጋ መከላከያ አልባሳት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት ጨረታውን መሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

1.     ተጫራቾች አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናችውን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት የሚያቀርቡ፣ ግብር የመፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ በግብር ሰብሳቤ ባለሥልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እንደዚሁም በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ እና መመዝገባቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።

2.     ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ለእያንዳንዱ ጫማዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡

3.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 40,000.00 ብር /አርባ ሺህ ብር/ በባንክ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙ ባንኮች በኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ስም በማሰራት ማቅረብ ይችላሉ፡፡ ከኢንሹራንስና ከፋይናንስ ተቋማት የሚቀርቡ ዋስትናዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማያያዝ አለባቸው፡፡

4.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሲዲ ኮፒ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከዚህ በታች በተገለፀው ቢሮ በመቅረብ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5.     ጨረታው ሰኔ 16 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ሰኔ 16 ቀን 2018 . ከጠዋቱ 430 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ በሚገኝበት ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ይከፈታል፡፡

6.     ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ሆነው ከተመረጡ የውል ማስከበሪያ የአሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል

7.     ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስፈር አለባቸው፡፡

8.     ኮርፖሬሽኑ በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

አድራሻ፡-

ቦሌ /ከተማ ወረዳ 05 ከመገናኛ አደባባይ ወደ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሚወስደው የቀለበት መንገድ ወደ ኢትዮጵያ ወጣቶችና ስፖርት ማእከል (አደይአበባ ስታዲየም) በሚያስገባው መገንጠያ መንገድ አጠገብ አዲሱ መሶብ የእንድ ማእከል አገልግሎት የሚሰጥበት ህንጻ

 

ስልክ ቁጥር፡- +251 118720722

አዲስ አበባ

 

የኢትዮጵያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን

 

Save Tender