የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ፣ የመኪና ገጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕግ/44/10/2018
1. የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ ጎማና ባትሪ፣ የመኪና ገጣጌጥና አልባሳት - እንዲሁም ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ በጨረታ መለያ ቁጥር ፌ.ቤ.ኮ/ብ.ግ.ጨ/ዕግ/44/10/2018 ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
2. ኮርፖሬሽኑ ለሚፈጽመው የተሽከርካሪ መለዋወጫ ጎማና ባትሪ የመኪና ጌጣጌጥና አልባሳት እንዲሁም ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪከ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነዳቸውን እና የዋጋ ሰነዳቸውን በሁለት ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
3. ጨረታው የሚከናወነው በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ሥነ-ሥርዓትና ይኸንን አስመልከቶ መመሪያ ቁጥር1070/2017 በፈዴራል መንግሥት ባለቤትነት የተያዙ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች የግዥ አፈጻጸም መመሪያ መሠረት ሲሆን ከሚፈለገው አገልግሎት ጋር የተዛመደ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይማስረጃ የሚያቀርቡ መሆን ይኖርበታል።
4. የተሟላ የአማርኛ የጨረታ ሰነዶችን ማንኛውም ፍላጎት ያለው ተጫራች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለገሀር በሚገኘው በቀድሞ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 209 በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶቻቸውን በኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ሁለተኛ ፎቅ ለዚሁ ታሽጎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በመጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ወይም ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓም ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ እንዲያቀርቡ ሆኖ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም ቢድ ቦንድ ጋራንት በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስም ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ሎት |
የሰነድ ዓይነት |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
ሎት 1 |
የተሽከርካሪ መለዋወጫ |
40,000.00 |
|
ሎት 2 |
የመኪና ጎማና ባትሪ የመኪና ጌጣጌጥና አልባሳት |
30,000.00 |
|
ሎት 3 |
ለመኪና ጥገና ሥራ የሚያገለግሉ የተለያዩ የኤሌክትሪክ እና ተዛማጅ ዕቃዎች ግዥ |
20,000.00 |
1. ዘግይቶ የቀረበ የጨረታ ሰነድ ውድቅ ይደረጋል፣ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት የኮርፖሬሽኑ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬከተር 2ኛ ፎቅ ይከፈታል።
2. በሚያወጣው ፕሮግራም መሠረት አሸናፊው ተጫራች በኮርፖሬሽኑ በግንባር በመገኘት ዕቃውን ያስረከባል፡፡
3. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-1-855-36-17 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን
