ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና መሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 011/2018 ዓ.ም
ፐብሊክ ሠርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሎት 1 ቱብለስ ጎማ የሀገር አቋራጭ አውቶቢስ 295/8R22.5፣ የከተማ አውቶቢስ ሽቦ ጎማ የኋላ 1200R200 እና የከተማ አውቶቢስ ሽቦ ጎማ የፊት 1200R200 መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 2 አቴዳንስ ማሽን መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 3 15 ሜትር መንገድ ግንባታ (15m asphalte road, extension road & guest parking/akaki site) A (Parking entrance gate-2 & remaining/ Yeka site) አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡
ሎት 4 ያገለገሉ የሽቦ ጎማ 12*20፣ ያገለገሉ የክር ጎማ 12*20 እና ያገለገሉ ቲዩብለስ ጎማ መሸጥ ይፈልጋል።
ሎት 5 ያገለገሉ ጠረጴዛዎች እና ወንበሮች መሸጥ ይፈልጋል፡፡
1. ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሠነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር የስራ ቀናት ከሎት 1 እስከ ሎት 5 ለእያንዳንዱ ሎት 500 በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 በአካል በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
2. ከሎት 1 እስከ ሎት 3 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና፣ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የብቃት ማረጋገጫ እና የአቅራቢዎች የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆነ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያለቸው፣ ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ከሎት 4 እስከ ሎት 5 ተጫራቾች በዘርፉ ንግድ ምዝገባና፣ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና የንግድ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፤ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የሎት 1 እና 3 ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሁለት ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ለሎት 4 እና ሎት 5 ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሠነድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ በአንድ ፖስታ በማዘጋጀትና በኢንቨሎፕ በማሸግ የድርጅቱ ማህተም ተደርጎበት ኃላፊነት በተሰጠው አካል ተፈርሞበት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
6. ተጫራቾች ለሎት 1፣ 2 እና ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 2% ሲፒኦ /Bid Bond/ ወይም በባንክ የተመሰከረለት በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች ለሎት 4 እና ሎት 5 የጨረታ ማስከበሪያ 20,000 (ሃያ ሺህ) ብር ሲፒኦ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
8. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 28 ይከፈታል፡፡ የጨረታ መክፈቻው ቀን የዕረፍት ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ ወይም በዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታ እና ሰዓት ይከፈታል፡፡
9. አገልግሎታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ይሁን ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡ የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት ከሜክሲኮ ወደ ልደታ ቤተክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ ፖሊስ ሆስፒታል ፊት ለፊት ነው
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ፡- 011-5-50-45-64
ፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት አገልግሎት
