የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት-1 የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች)፣ የጽዳት አገልግሎት ግዥ እና በሎት-2 የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ ለአንድ ዓመት የሚቆይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፤ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEPNP/NCB/27/2018
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሎት-1 የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች)፣ የጽዳት አገልግሎት ግዥ እና በሎት-2 የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ ለአንድ ዓመት የሚቆይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፤ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገፅ (e-GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለባቸው፡፡
2. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፤
3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. ተጫራቾች በሎት-1 የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች)፣ የጽዳት አገልግሎት ግዥ እና በሎት-2 የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ አገልግሎት ግዥ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/27/2018 የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
|
ቁጥር |
የግዥ አይነት Descriptio |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ |
የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት |
|
ሎት 1 |
የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ(ዲች) የጽዳት አገልግሎት ግዥ |
ብር 12,000.00 (አስራ ሁለት ሺህ ብር) |
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ. ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሰኔ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
|
ሎት 1 |
የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ አገልግሎት ግዥ |
215,000 (ሁለት መቶ አስራ አምስት ሺህ ብር) |
5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-06-27 መደወል ይችላሉ፡፡
6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
