Tender Detail

Tender Details


በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ ቅ/ጽ/ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና

ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታስታወቂያ ቁጥር 02/2019

 

በአዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ //ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በሀራጅ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን ሞባይሎች፣ የሞባይል ከፍሎች፣ የኤሌከትሮንክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፥ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃና መስፈርቶች ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ሐምሌ 16/2018 . ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይየሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም:-

1.     በተሸከርካሪ ሀራጅ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O) ጨረታው ከመጀመሩ አስቀድሞ በማስመዝገብ በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።

2.     በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታከስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቬሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

3.     በጨረታው ላይ የተሸከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም፡፡

4.     ተጫራቾች የተሽከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ሐምሌ 16/2018 . ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ//ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

5.     በዕቃ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በቅ//ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6.     የዕቃና የተሸከርካሪ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ወይም ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) በተ. 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን፡፡

7.     ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ፡፡

ተ.ቁ

የቅ/ጽ/ቤቱ ስም

የጨረታ አይነት

የንብረታ መመለከቻ ቀን የቸረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታዉ መዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

.አ ቃሊት ጉምሩክ ቅ/ ጽ/ቤት

የኢቃ ግልፅ

እስከ 21/11/2018

22/11/2018 3፡45 ተዘግቶ በዚያዉ ቀን 4፡00 ሰኣት ይከፈታል።

የተሽከርካር ሐራጅ

እስከ 21/11/2018      

22/11/2018 4፡00 በዚያዉ ቀን 4፡00 ሰዓት ይጀመራል።

 

8.    የጨረታው መከፈቻ ቦታ፡ . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራffi ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል፡፡

9.    ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

10.  አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል፡፡

11.                        ከላይ በተ/ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱተጫራቾችለጨረታ ማስከበርያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል፡፡

12.                        /ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-አዲስ አበባ ቃሊት ጉምሩከ :- 011-470 - 85 03

አድራሻ፡- ሳሪስ አቦ / በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው ወደ ኮዬ ፈጬ መንገድ መንገጠያ ፊት ለፊት ያለው ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

 

በአዲስ አበባ ቃሲት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

Save Tender