Tender Detail

Tender Details


የጅማ ከተማ ገንዘብ ጽ ቤት በ2019 በጀት ዓመት በጅማ ከተማ መስተዳደር ስር ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች እና ለጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል::


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የጅማ ከተማ ገንዘብ ቤት 2019 በጀት ዓመት በጅማ ከተማ መስተዳደር ስር ለሚገኙ መስሪያ ቤቶች እና ለጅማ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ

1. የጽህፈት መሳሪያ፤

2. የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ፤

3. የጽዳት መሳሪያ፤

4. የተለያዩ የመኪና እና የማሽነሪ ጎማዎችን፤

5. የደምብ ልብሶች

6. የተለያዩ ሞተር ሳይከሎች እና

7. የቢሮ እቃዎችን (Furniture) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡-

ስለሆነም

1. በተጠቀሱት የስራ አይነቶች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን (2018) ግብር የከፈሉና ንግድ ፈቃዳቸውን 2019 የስራ ዘመን ያሳደሱ እና የታደሰውን ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. ተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. TIN እና VAT ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና TAX clearance ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከጅማ ከተማ ፋይናንስ ቢሮ የማይመለስ ብር 1700 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ ተከታታይ በመንግስት የስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ለጨረታው ማስከበሪያ 100,000 (መቶ ሺህ) ብር ሲፒኦ በጅማ ከተማ ገንዘብ /ቤት ስም አሰርተው ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው (ለእያንዳንዱ ጨረታ)

6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻልና ቴክኒካሉን ኦርጂናሉንና ኮፒውን በመለየት በኢንቨሎፕ ታሽጎ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 የስራ ቀናት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይችላሉ፡፡

7. ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት እለት ጀምሮ 15 የስራ ቀን ሲሆን ይህ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው የመንግስት የስራ ቀን 830 ታሽጎ በዚሁ ቀን 900 ሰዓት ላይይከፈታል፡፡

8. በተባለው ቀንና ሰዓት ያልመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ሳይከፈት ለባለቤቱ ተመላሽ ይሆናል፡፡

9. የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን በራሱ ትራንስፖርት በጅማ ከተማ ገንዘብ /ቤት ወይም በተባለበት ቦታ ገቢ አድርጎ ገንዘቡን ይቀበላል።

10. በዚህ ማስታወቂያ የተጠቀሱት መስፈርቶች በሰነዱ ላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች ጋር የመጀመሪያ ዙር ቴከኒካል ግምገማ ነጥቦች ይሆናሉ፡፡

11. ጽህፈት ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡-

የጅማ ከተማ ገንዘብ /ቤት ቢሮ ቁጥር 8 አባ ጂፋር አደባባይ ጅማ ከተማ መስተዳደር ቅጥር ግቢ

Jimma city Administration yard, Finance Office Building, Ground Floor ስተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር-0472114408 ደውሰው መጠየቅ ይችሳሱ።

 

የጅማ ከተማ ገንዘብ /ቤት

 

Save Tender