Tender Detail

Tender Details


በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ሰሜን ሸዋ ዞን የያያ ጉለሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች ጥራቱን የጠበቀ የተለያዩ የግንባታ እቃዎች በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ሰሜን ሸዋ ዞን የያያ ጉለሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለ2019 በጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙት የመንግስት መ/ቤቶች ጥራቱን የጠበቀ የተለያዩ

1.     የጽህፈት መሳሪያዎች፤ አላቂ የቢሮ እቃዎች እና የጽዳት መሳሪያዎች

2.    የደንብ ልብሶች

3.    ቋሚ የቢሮ እቃዎች ፈርኒቸር/

4.    የተለያዩ ኤልክቲሮኒክሶችና የመኪና ጎማዎች፤ የሞተር ዘይት፤ የግንባታ እቃዎች

በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጨራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።

1.     በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና ገንዘብ ሚኒስንቴር ባወጣው ለአቅራቢነት የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ

2.    ማንኛውም የጥቃቅን አነስተኛ እና ለሎችም ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) 40,000 (አርባ ሺህ ብር) (በካሽ 40,000 Birr) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

3.    የጨረታው ሰነድ የማይመለስ 300.00(ሦስት መቶ ብር) በመከፈል ከቢሮ ቁጥር 03 ቀናት በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሚቆጠረው 21 የስራ ቀናት በመቅረብ መግዛት ይችላል።

4.    ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋና እና ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.    ዋጋው የትራንስፖርት ፤ የማውረጃ እና መጫኛ ወጪ ጨምሮ የሚሸጥበትን በሰነዱ ላይ ተሞልቶ ይቀርባል።

6.    ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ 22ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ ቀን ልክ በ 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7.    መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

8.    የጨረታው የመክፈቻ ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ እና ከላንደር የሚዘጋበት ቀን ላይ ከዋለ በቀጣይ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0988436921 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።

 

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳደር ሰሜን ሸዋ ዞን የያያ ጉለሌ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

 

 

Save Tender