Tender Detail

Tender Details


በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆን እስቴሽነሪና የጽዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የጽዳት እቃ፤ የተሽከርካሪ ጎማ፤ የግንባታ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ

ማስታወቂያ መለያቁጥር GGWW/0001/2019

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ከልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2019 በጀት ዓመት በመደበኛ በጀት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚሆን እስቴሽነሪና የጽዳት እቃ፤ ኤሌክትሮኒክስ፤ የጽዳት እቃ፤ የተሽከርካሪ ጎማ፤ የግንባታ እቃዎች በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም ለግዢ የቀረቡ እቃዎችና የጨረታ ማስከበሪያ CPO

1.    ሎት አንድ ፡ እስቴሽነሪና የጽዳት እቃ ፤ የጨረታ ማስከበሪያ 40000 ብር

2.    ሎት ሁለት ፡ ኤሌክትሮኒክስ ፣ የጨረታ ማስከበሪያ 20000 ብር

3.    ሎት ሶስት ፡የተሽከርካሪ ጎማ፡ የጨረታ ማስከበሪያ 30000 ብር

4.    ሎት አራት የግንባታ እቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ 20000 ብር ስለሆነም ተወዳዳሪዎች፡

5.    የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫትና የቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

6.    የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን online ሲስተም የተመዘገበ መሆን አለበት።

7.    በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆነ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መምጣት አለባቸው።

8.    ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት 6፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 300 ብር/ሶስት መቶ/ ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች የጨረታውን ቴክኒካልና ፋይናንሺያል ዶክመንት ሲያቀርቡ፤ ሀ/ለቴክኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴክኒካል በሚል በመለየት እናለ/ ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል ና ሁለት ፎቶ ኮፒውን ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ የተጠቀሱት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴክኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም ሁሉንም በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ፋይናንሻል ዶክመንት በሚል በመለየት ፡ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20 /ሃያ/ ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ከገ/ጉ/ወ/ወ ፋይናንስ ጽ ቤት ቢሮ ቁጥር 3 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9.    የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም መሰራት አለበት።

10.        የጨረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀናት ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ ከቀኑ 8፡30 ደግሞ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

11.        መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ማሳሰቢያ፡

1.    በግዢ ኤጀንሲ በዕቃ አቅርቦት ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶችም መወዳደር አይችሉም

2.    የቫት 7.5 ለወረዳ ገቢ የሚቆርጥ

3.    ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፏቸው እቃዎች የጥራት ችግር ያለባቸው መሆናቸው በቴክኒክ ጥራት ኮሚቴ ከተረጋገጠ ተመላሽ መሆናቸውን እናስታውቃለን፡፡

4.    ተጫራቾች ተጫርተው ያሸነፉዋቸው ማንኛውም እቃዎች የወረዳው ማዕከል ማለትም ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መሀል አምባ ማቅረብ ያለባቸው ሲሆን የወረዳው ማእከል ርቀት ከአዲስ አበባ 116 - ኪ.ሜ ነው።

5.    ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

ለበለጠ መረጃ 0113360631 / 0113360146

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር

 ወለኔ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender