በቂርቆስ ከፍለ ከተማ ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የህከምና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የህፃናት መጫወቻ ዕቃዎች፤ የላቡራቶሪ ዕቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ከፍለ ከተማ ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2019 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ ቋሚ ዕቃዎች፣ የፅህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣የፅዳት ዕቃዎች፣ አላቂ የህከምና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የህፃናት መጫወቻ ዕቃዎች፤ የላቡራቶሪ ዕቃዎችና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆንም የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ የምታሟሉ ተጫራቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
1. የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑ ግብር የከፈሉ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. በመንግስት ንብረት ግዥ አስተዳደር ኤጄንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (vat) ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡
5. ከሊራንስ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ከግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ስለ ግብር እከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
6. የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 2% (ሁለት ፐርሰንት) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀና ለዚህም ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በመከፈል የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን(ግዥ ከፍል) ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ፡፡
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ 15% ቫትን ጨምሮ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ - ማቅረቢያ በግልፅ መሙላት አለባቸው ይህን ያላደረጉ ተጫራቾች ቫትን አካተው እንደሞሉ ይቆጠራል፡፡
10. ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰአት በ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
11. ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ላይ በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
12. ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ካዛንሽስ ቶታል ፊት ለፊት ወደ አዋሬ መሄጃ መንገድ ምስ ጎህ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር፡- 0115-15-56-52
ምስራቅ ጎህ ስጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
