Tender Detail

Tender Details


በአርሲ ዞን የመርቲ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና የነበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የጨረታ ማስታወቂያ

-01/2019

 

በአርሲ ዞን የመርቲ ወረዳ ገንዘብ /ቤት 2019 የበጀት ዓመት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መሥሪያ ቤቶችና የነበሌ አስተዳደሮች አገልግሎት የሚውሉ ሎት1 ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ፣ ሎት2 የሠራተኞች የደንብ ልብስ (ሎት3. የጽህፈት መሳሪያዎች፡፡ ሎት4. የጽዳት እቃዎች ሎት5 ፈርኒቸር በግልጽ ጨረታ እወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡

1.     ለተጠየቁት የግዥ ዕቃዎች ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ከፍለው የንግድ ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (Tax payer Registration No)! የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በፌዴራል፣ በክልል ወይም በዞን ገንዘብ /ቤት ወይም በግዥዎችና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው ዋናውንና ኮፒውን ማስረጃማቅረብ የሚችሉ፡፡

2.    ተጫራቶች ለቋሚ የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ እቃዎችና ለጽህፈት መሳሪያዎች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ) (ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለጽዳት እቃዎች እና ለደንብ ልብስ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ) በመርቲ ወረዳ ገንዘብ /ቤት ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000075175648 ገበ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጽ/ቤቱ የግዥ ንብረት አስተዳደር ማስወገድና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ቁጥር : በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

3.    ተጫራቾች ከግብር ሰብሳቢው /ቤት የዘመኑን ግብር አጠናቀው ለመከፈላቸው እና ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን ደብዳቤ ማቅረብ አለባቸው፡፡

4.    ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የዋጋ ማቅረቢያ ሠነድ በመሙላት በዝግ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው የሥራ ቀናት ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ጨረታው 16ኛው የሥራ ቀን 400 ሠዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት 430 ሠዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጽ/ቤቱ ቅፅር ግቢ በተዘጋጀው ቦታ ፖስታው ይከፈታል፡፡

5.    ማንኛውም ተጫራች ለቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ለጽህፈት መሳሪያዎች የጨረታ ሰነድ ማስከበሪያ ብር 40000.00(አርባ ሺህ) ለደንብ ልብስ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር20000.00 (ሃያ ሺህ) እንዲሁም ለጽዳት እቃዎች እና ለቋሚ የቢሮ ፈርኒቸር እቃዎች ለእያንዳንዱ ሰነድ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 10000.00 (አስር ሺህ) በአቅራቢያችሁ በሚጎኝ የታወቀ ባንከ በክፍያ ማዘዣ (CPO)ብቻ ማቅረብ አለባቸው::

6.    አሸናፊው ተጫራች ያለምንም የአቅርቦት ችግር አስተማማኝ የሆነ የዕቃ ከምችት ያለውና ዕቃዎቹን በራሱ የማጓጓዣ ወጪ አቦምሳ ከተማ በሚገኘው የወረዳው ገንዘብ /ቤት ድረስ አምጥቶ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡

7.    /ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ .ቁጥር 0922073769, 0913395762, ይጠይቁ፡፡

 

በአርሲ ዞን የመርቲ ወረዳ ገንዘብ /ቤት

 

Save Tender