Tender Detail

Tender Details


የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅንና በስሩ ለሚገኙ ሁሉም ቅጽ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ የስቴሽነሪ ዕቃዎችን፤ የጽዳት እቃዎችን፣ የህትመት አገልግሎት፤ የመኪና ቅባቶች፣ የመኪና እቃዎች፣ ፕላንትና ማሽነሪ እና የህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።


የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር-PSSSA/AAR/01/2019

 

የመንግሥት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅንና በስሩ ለሚገኙ ሁሉም ቅጽ/ቤቶች አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የደንብ ልብስ፣ የስቴሽነሪ ዕቃዎችን፤ የጽዳት እቃዎችን፣ የህትመት አገልግሎት፤ የመኪና ቅባቶች፣ የመኪና እቃዎች፣ ፕላንትና ማሽነሪ እና የህንፃ ቁሳቁስና ተገጣጣሚ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው ለመወዳደር የምትፈልጉ የሃገር ውስጥ ተጫራቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላትይጠበቅባችኋል።

1.     ተጫራቾች ህጋዊና በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት፣ ጊዜው ያላለፈበት የነቢዎች ከሊራንስ ደብዳቤ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ምስከር ወረቀት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባችሁ።

2.     ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10/አስር/ተከታታይየስራ ቀናት ውስጥ ፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ጀርባ ከሚገኘው የሪጅኑ /ቤት ዋስትና ንግድ ማዕከል ህንፃ ግራውንድ ሰው ሃብት አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 16 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 200(ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

3.     በመ/ቤተችን ስምማለትም_ public servant social security administration AA region/PSSSA AA region/ የተሰራ የጨረታ ማስከበሪያ በአንድ ሎት ብር 3.000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ

4.     ስቴሽነሪ፣ ፅዳት፣ /ልብስ እና_የመኪና ቅባትና እቃዎች ላይ የሚወዳደር ተጫራች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ እቃ አንድ ሳምፕል ጨረታው ከወጣ እስከ 10ኛው ቀን ድረስ ለግዥ ከፍሉ ሳምፕል ማቅረብ አለባችሁ።

5.     ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ሰነድ በመሙላት 10 የስራ ቀን ውስጥ ከጠዋቱ 200 እስከ 1100 ድረስ ሰነዱን በዝዙበት የሪጅኑ /ቤት በመምጣት አሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ ለየብቻው በማሸግ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውንም ለብቻው በማሸግ ሶስቱን ፖስታዎች በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ አሽገው የድርጅቱን ስም፣ መሃተምና ፈርማ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

6.     የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ ልከ 315 ሰዓት ሲሆን የሚከፈተውም በዚሁ ዕለት 330 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት/ባልተገኙበት ይሆናል።

7.     11ኛው ቀን የበዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።

8.    መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ስልክ ቁጥር አድራሻ፡- 011-1-11-23-13

 

የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር አዲስ አበባ ሪጅን

 

 

 

✨ messages.ai_summary
The Government Employees Social Security Administration, Addis Ababa Region, invites local bidders to an open tender (Ref No. PSSSA/AAR/01/2019) for uniforms, stationery, cleaning supplies, printing services, vehicle lubricants and parts, plant and machinery, and building materials and fixtures. Bid documents cost a non-refundable 200 ETB, and a bid bond of 3,000 ETB per lot is required via confirmed CPO. Submission deadline and bid opening are on 2026-08-11. Bidders must provide a valid renewed business license, tax clearance certificate, supplier registration, and VAT certificate; those bidding on stationery, cleaning supplies, uniforms, or vehicle lubricants/parts must submit samples by the 10th day.
Save Tender