አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመደበኛ በጀት ለመግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001/2018
አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ በመደበኛ በጀት ለመግዛት ይፈልጋል። ሎትı የደንብ ልብስ እና ስፌት ሎት2. የፅህፈት መሣሪያ(አላቂ የቢሮ እቃ) ሎት 3 የህትመት ስራ ሎት4.የትምህርት መርጃ ዕቃዎች ሎት5.የፅዳትዕቃ.ሎት6 የህንፃ፤የኤሌክትሪክ ዕቃዎችን ሎት7. ማሽነሪ ጥገናና ግብዓቶች ሎት8. ቋሚ ዕቃ ሎት9. ለህንፃ ጥገናና ግብዓቶች ዕቃ ሎት10. አላቂ የህከምና ዕቃ ሎትክ የሰራተኛ መስተንግዶ ሎትı2 የትራንስፖርት አገልግሎት የመሳሰሉትን በጨረታ ማወዳደር ይፈልጋል። ሰለሆነም በጨረታው ለመሣተፍ የምትፈልጉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
1. የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ምዝገባ ምስከር ወረቀት
2. በዘርፉ የተሰማሩበት ፍቃድ በዕቃ አቅራቢነት እና አገልግሎት በፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮየተመዘገበ እና የግብር ከፋይ መለያ(Tin) እና የተጨማሪ እሴት ታከስ (ቫት) ተመዝጋቢየሆነ።
3. ጨረታውን ለመሳተፍ በቅድሚያ ለተጠቀሱት እቃዎች የማይመለስ በሎት ብር 100.00 (አንድመቶብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በቢሮ ቁጥር 3 በመቅረብ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዶቻቸውን ኦርጂናል እና ፎቶኮፒ ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጅው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን በግልፅ ማስቀመጥ አለበት።
5. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ከጨረታው መከፈቻ ቀን በፊት ናሙና የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።በተጨማሪም ተወዳዳሪዎች ዋጋ የተሞላበት ቋሚ ዕቃን በፎቶ ከዛ ውጭ ያሉትን እያንዳንዱ ሎቶች ናሙና ማቅረብ ግዴታ ነው ካልሆነ ግን ተጫራቶች ከጨረታው ውጪ ይሆናል።
6. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው እቃዎች በተናጠል በየሎቱ ለሎትነብር 33.982.80
ለሎት2ብር 4,073.58 ለሎት3 ብር2.995.32 ለሎት4 ብር 24,134.36 ለሎት5 ብር36.716.72 ለሎት6 ብር 5000 ለሎት7 ብር 2000 ለሎት 8 ብር 22,279.98 ለሎት9 ብር 2,200 ለሎት10 ብር 800 ለሎትከብር 29,648 ለሎት12 ብር 4,400 የጨረታ ዋስትና ቢያንስ ለስድስት ወር ፀንቶ የሚቆይ በባንክ የተረጋገጠ የጨረታ ማስከበሪያ ሲ.ፒ.ኦ እስከ ጨረታ መዝጊያው ቀን ድረስ ከዋና ሰነዱ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
7. ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እስከ 10 ተከታታይ የስራ ቀን ድረስ የሚቆይ ሲሆን በእሥረኛው ቀን ከሰዓት በኋላ 11፡00 ስዓት ተዘግቶ በአስራንአደኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ ፋይናንስ/ግ/ን/አስ/ገ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 3 ይከፈታል።
8. አሸናፊ ድርጅት የተገዙትን(የታዘዙትን)እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ተቋሙ ድረስ በማቅረብ ገቢ ማድረግ አለበት።
9. የጨረታው አሽናፊ ድርጅት ውል ከመፈረማቸው በፊት የውል ማስከበሪያ 10%ማሲያዝ ይጠበቅባቸዋል።
ማሳሰቢያ፦ ት/ቤቱ በጨረታ ሰነድ ውስጥ የተጠቀሱትን እቃዎች ካለው በጀትና (የተሻለ መንገድ ካገኘ) እንዲሁም በሎሎች ተያያዥ ጉዳዩች ጋር በተያያዘ የዕቃዉን ብዛት 20% የመጨመር፤የመቀነስ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው።በተጨማሪም የጨረታ ማስከበሪያ የማያሲዙ ተጫራቾች እሴት የሚጨምሩ (እምራች ሲሆኑ ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾት ካደራጃቸው አካል በሚያመጡት ደብዳቤ ይስተናገዳሉ። አድራሻ፡-በጉለሌ ክ/ከተማ ቀጨኔ በድሮ ወረዳ 5 ባሁኑ ወረዳ 4 ከፍ ብሎ ቀበሌ 07/17መዝናኛ ከበብ ወደ ውስጥ 100 ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ በት/ቤቱ ስልክ ቁጥር፡- 0111568312 ይደውሉ
አዲስ ብርሃን ቅ/አንደኛ/አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
