የጽህፈት መሣሪያና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ
የጨረታ ማስታወቂያ
የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በዞኑ ለሚገኙ ሴከተሮችና መምሪያዎች የሚያስፈልጉ የተለያዩ ዓይነት፡-
- ሎት 1 - የጽህፈት መሣሪያና
- ሎት 2 - የጽዳት ዕቃዎች
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት ተጫራቾች:-
- በመስኩ የታደሰ ንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር
- የቫት ተመዝጋቢነት ሠርትፍኬት
- የዕቃና አገልግሎት አቅራቢነት ሰርትፍኬት ያላቸው ድርጅቶች፤ በሀድያ ዞን ፋ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 17 በአካል በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ብር 100/አንድ መቶ ብር/ በመክፈል እንድትገዙና ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሎት-1 30,000 ሎት -2 20,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ማስያዝ የሚጠበቅባቸው ሲሆን የጨረታ መወዳደሪያ መምሪያው ባዘጋጀው ፎርማት ላይብቻ በመሙላት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይቀናት የመወዳደሪያ ፖስታዎችን ኦርጅናልና ኮፒ በማሸግ ቢሮ ቁጥር 17 ላይ በሚገኘው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እንድታስገቡና ጨረታውም በ16ኛው ቀን ከሠዓት 8፡00 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥን ታሽጎ በ8፡30 ላይ የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የእረፍት ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
መሥሪያ ቤቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0461784281 /0465552337 ደውሎ መጠየቅ የሚቻል መሆኑን እንገልጻለን፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት የሀድያ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
✨ messages.ai_summary
- The Hadiya Zone Finance Department, under the Central Ethiopia Regional State, invites open tenders for Lot 1: office stationery and Lot 2: cleaning supplies for zone sectors and departments.
- Bid documents are available at office no. 17 for ETB 100; bids must be submitted within 15 consecutive days from the announcement date.
- The bid bond is ETB 30,000 for Lot 1 and ETB 20,000 for Lot 2, in the form of a bank-confirmed CPO.
- Bidders must hold a renewed trade license, tax identification number, VAT registration certificate, and goods/service supplier certificate.
- The tender box closes on the 16th day at 8:00 and opens at 8:30; if that day falls on a holiday, it moves to the next working day at the same place and time.
