Tender Detail

Tender Details

  • Company የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስና/ኢኮ/ስ/መም/ያ
  • Address Hawasa, Phone: 046-212-13-34
  • Website
  • Deadline19 Aug 2026, 9:30 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Priceብር 500 (አምስት መቶ ብር)
  • opening dateበ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
  • Categories Cleaning & Janitorial , Office Supplies And Services

የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ


የጨረታ ማስታወቂያ

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ለ23ቱም ሴክተር መስሪያ ቤቶች በ2019 በጀት ዓመት በታቀደው መሰረት የጽህፈት መሳሪያዎች እና የጽዳት ዕቃዎች ግዥ ለመፈጸም በግልጽ ጨረታ በማወዳደር በዘርፉ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች መካከል በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሠረት -

  • የጽህፈት መሳሪያዎች ግዥ:- ሎት: 01/2019
  • የጽዳት ዕቃዎች-ሎት 02/2019

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር ይችላሉ፡-

  1. በሥራ መስኩ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መከፈላቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  3. ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣
  4. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፣
  5. ከሚመለከተው መ/ቤት የታክስ ከሊራንስ ማቅረብ አለበት፤
  6. የጨረታ ሰነዱን ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ (አዲሱ ከተማ አስተዳደር ህንፃ) አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 54 (ሃምሳ አራት) በመቅረብ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ1ዐ /ለአሥር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቀርባችሁ ሰነድ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (የተመሰከረ) ሲ ፒ አ (CPO) ወይም ቢድ ቦንድ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
  8. ጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቬሎፕ አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ፋይናንሻል በመያዝ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 (አሥር) ተከታታይ ቀናት ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 54 (ግዢ ኬዝ ቲም) ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ሆነ ባልተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በቢሮ ቁጥር 54 ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን በበዓላት ፤ቅዳሜ ወይም እሁድ ከሆነ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
  10. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ስልክ ቁጥር 046-212-13-34

የሀዋሳ ከተማ አስ/ፋይ/ኢኮ/መምሪያ

✨ messages.ai_summary
Hawassa City Administration Finance and Economic Cooperation Department is procuring office supplies (Lot 01/2019) and cleaning materials (Lot 02/2019). Bid documents cost 500 ETB, and a bid bond of 100,000 ETB per lot (bank-guaranteed CPO or bid bond) is required. Bids close on the 11th day at 3:30 AM and open at 4:00 AM; documents are purchasable within 10 consecutive days. Eligible bidders must have a valid renewed trade license, business registration certificate, proof of current tax payment, VAT registration, supplier registration certificate, and tax clearance.
Save Tender